ምርጫ ቦርድ መመሪያ አንቀጽ 16/2‘ን ሰረዘ

Views: 115

ምርጫ ቦርድ ለዕጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ፣ ድጋፍ ፊርማ አሰባሰብ እና የመለያ ምልክት አመራረጥ ካወጣው መመሪያ አንቀጽ 16/2‘ን እንደሰረዘ ኀሙስ፣ የካቲት 18 በፌስቡክ ገጹ ባሰራጨው መግለጫ አስታውቋል፡፡ አንቀጹ የመንግሥት ሠራተኞች ለምርጫ ዕጩነት ለመቅረብ ሥራቸውን እንዲለቁ እንደማይገደዱ፤ ዕጩ ከሆኑ በኋላ ደሞ ያለ ደመወዝ ፍቃድ ወስደው የመወዳደር መብት እንዳላቸው የሚደነግግ ነው፡፡ ሆኖም በተለያዩ ምርጫ ክልሎች አንቀጹን በተሳሳተ መንገድ በመተርጎም፣ የመንግሥት ሠራተኞች በዕጩነት ለመመዝገብ ያለ ደመወዝ ፍቃድ የወሰዱበትን ሰነድ እየተጠየቁ በመሆኑ አንቀጹን ሰርዠዋለሁ- ብሏል ቦርዱ፡፡


ቅጽ 2 ቁጥር 121 የካቲት 20 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com