የምርጫ ቃላት ፍቺዎች

Views: 137

የምርጫ ክልል/የምርጫ ወረዳ

  • የምርጫ ክልል ወይም በተለምዶ የምርጫ ወረዳ እየተባለ የሚጠራው ለተወካዮች ምክር ቤት ወይም የክልል ምክር ቤት መቀመጫ የሚመረጥበት ነው፡፡ የተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ በህገመንግስቱ የተወሰነ ሲሆን የክልል ምክር ቤት እና የከተማ መስተዳድር መቀመጫዎች ደግሞ በክልሎች ህግ መሰረት የሚወሰኑ ናቸው፡፡

የምርጫ ጣቢያ

  • ዜጎች የሚመርጡበት እና ድምጽ የሚሰጡበት ቦታ ማለት ነው፡፡

አገር ውስጥ ታዛቢ

  • በሲቪል ማኅበራት ኤጀንሲ የተመዘገበ አገር በቀል የሲቪል ማኅበር ድርጅት ሲሆን ምርጫን ከመታዘብ ወይም ተያያዥ ሥራ ላይ የመሰማራት ሥራ የሚሰራ እንዲሁም ቦርዱ የመታዘብ ጥሪ ሲቀርብ መስፈርቱን አሟልቶ የተመዘገበ ድርጅት ነው፡፡

ዓለም አቀፍ ታዛቢ

  • ዓለም አቀፍ ታዛቢ ድርጅት በኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ምርጫ እንዲታዘብ ጥሪ የተደረገለት ዓለም አቀፍ ተቋም ነው፡፡

እጩ ተወዳዳሪ

  • የግል ወይም የፖለቲካ ፓርቲ ባመለከተው የምርጫ ተወዳዳሪ ለመሆን የተመዘገበ እና መታወቂያ ያለው ግለሰብ ሲሆን ምዝገባው የሚፈጸመው በምርጫ ክልል ቢሮዎች ነው፡፡

ምርጫ አስፈጻሚ

  • ምርጫ አስፈጻሚ ማለት ምርጫን ለማስፈጸም ለአጭር ጊዜ የሚመለመል እና ስልጠና የሚሰጠው ግለሰብ ሲሆን የምርጫ ቦርድ ቋሚ ሰራተኛ አይደለም፡፡

ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ


ቅጽ 2 ቁጥር 121 የካቲት 20 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com