የሩብ ክፍለ ዘመን ጉዞ

Views: 140

ባሳለፍነው ሐሙስ የካቲት 18/2013 የዳሽን ባንክ 25ኛ ዓመት የብር እዩቤልዩ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱን በሸራተን አዲስ ሆቴል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) በተገኙበት በይፋ ጀምሯል፡፡
ባንኩ 1988 ሲመሰረት በ50 ሚሊዮን ብር የተፈቀደ ካፒታል በ10 ቅርንጫፎች እንደነበር ያስታወሱት ፕሬዝዳንቱ 25ኛ ዓመቱን ሲያከብር ከ450 በላይ ቅርንጫፎች መድረሱን ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ጠቅላላ ሀብቱ 67 ቢሊዮን ብር ደርሷል ብለዋል፡፡
ባንኩ በአፍሪካ ተወዳዳሪ ባንክ ለመሆን በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር በመከተል ግስጋሴውን እንደሚቀጥል ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል፡፡
የብሔራዊ ባንክ ገዢው በበኩላቸው ዳሸን ባንክ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት ባንኮች በብሔራዊ ባንክ ምዘና ከአንድ እስከ ሦስተኛ ደረጃ የሚቀመጥ ባንክ መሆኑን ጠቅሰው፣ ከአፍሪካ ባንኮች ከአንድ እስከ አስረኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ በርትቶ መሥራት አለበት ብለዋል፡፡


ቅጽ 2 ቁጥር 121 የካቲት 20 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com