ፌስ ቡክ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ነክ ማስታወቂዎች ላይ ግልጽነት እንዲላበሱ አደረገ

Views: 251

በሰፊ ማኅበራዊ ትስስር ገጽነቱ የሚታወቀው ኩባንያ ፌስ ቡክ በኢትዮጵያ ግልጽነት የተላበሰ የፖለቲካ ነክ ማስታወቂያዎችን በማኅበራዊ ገጹ ላይ ማስጀመሩን አስታወቀ። ኩባንያው በመጪው ግንቦት የሚካሔደውን አገራዊ ምርጫን ታሳቢ በማድረግ ነው ይህን የፖለተካ ነክ ማስታወቂያዎች በፌስ ቡክ ትስስር ገጽ ላይ ያስጀመረው።
ፌስ ቡክ ኩባንያ የተለያዩ አይነት ጅማሮዎችን ያስጀመረ ሲሆን በተለይም ደግሞ ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ ግልጽነትን ለማላበስ እንዲሁም ሕብረተሰቡን በማብቃት እና ስለ ማኅበራዊም ሆነ ፖለቲካዊ ጉዳዮች በጥቂቱም ቢሆን መረዳት እንዲኖረው የታሰበ መሆኑ ታውቋል። ከዚህም ጋር በተያያዘ ግለሰቦች በግል ፌስ ቡክ አካውነታቸው ላይ በሚታዩ የፖለቲካ ነክ ማስታወቂያዎች ላይም ቁጥጥር ማድረግ እንደሚችሉ እና የማይፈልጉትን ወይም ከፍላጎታቸው ውጪ በክፍያ ሚተላለፉ ፖለቲካ ነክ ማስታወቂያዎችን ሰዎች ማየት የግድ እንደማይሆንባቸውም ነው ስለ አዲሱ አሰራር በፌስ ቡክ አፍሪካ ፖሊሲ ዲይሬክተር ኮጆ ቦአኪ የተናገሩት ። ከዚህ ቀደም የፖለቲካ ነክ ማስታወቂዎች በማን ይዘወሩ እንደነበር በግልጽ ይታወቅ ያልነበረ ሲሆን ይህ አሰራር ግን ግልጽነትን የሚላብስ እንደሚደርገው ታውቋል።
ይህ አይነት አሰራር በባለፈው የፈረንጆች ዓመት ላይ በበርካታ የዓለም አገራት ላይ ተግባራዊ የሆነ ሲሆን በቀጣይም ደግ ኢትዮጵያ እና ኬንያን ጨምሮ 98 አገራት ላይ ተግባራዊ እንደሚደረግ ለማወቅ ተችሏል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com