የእለት ዜና

‹‹ቆሜ ልመርቅሽ›› ጥላሁን ገሠሠን የሚዘክር ኮንሰርት በሸገር ወዳጅነት ፓርክ ተካሄደ

ኢትዮጵያን ‹‹ቆሜ ልመርቅሽ›› ያለበት የድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠ የሙዚቃ አልበም ከዳግማዊ ትንሳኤ በኋላ እንደሚለቀቅ ከትላንት በስቲያ በሸራተን አዲስ ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።
አልበሙ አገራዊና የፍቅር መልእክቶች የያዘ ሲሆን ከሞተ በኋላ አልበሙ ሊለቅ ታስቦ ግጥሞቹ በጊዜው የነበረውን መንግሥት ስለሚዳፈሩ ተፈርቶ ዘፈኑ ሳይለቀቅ አንደቆየ ተነግሯል።
የዛሬ 12 ዓመት በሞት የተለየው ድማፃዊ ጥላሁን ገሠሠ ከ 15 ዓመት በፊት ዘፍኗቸው ለሕዝብ ያልተሰሙ 10 ሙዚቃዎች በመሰብሰብ በባለሀብቱ ሼክ መሐመድ አላሙዲ አስተዋጽዖ ከፍተኛ እንደነበረ የተነገረ ሲሆኑ ሙዚቃዎቹ አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ እንዳቀናበራቸው ተጠቅሷል። ሰባቱን ሙዚቃች ያየህራድ አላምረው የገጠማቸው ሲሆን ዜማው ደግሞ ሞገስ ተካ እንደሠራው ተገልጿል።
ከፋሲካ በዐል በኋላም የዝከረ ጥላሁን ገሠሠ የሙዚቃ ኮንሰርት እንደሚኖር የተነገረ ሲሆን ጥላሁን ገሠሠ የሚከበርበትና የሚወደስበት የእራት ምሽት የሚዘጋጅ ሲሆን በዚህ ምሽት እያንዳንዳቸው ዐሥር ሰው የሚይዙ እና በአንድ ሚልዮን ብር የሚሸጡ 300 ጠረጴዛዎች እንደተዘጋጁ የተገለፀ ሲሆን ገቢውም ‹‹ከገበታ ለሀገር›› መርሃገብር እንደሚውል ተገልጿል።
በተያያዘም በክቡር አርቲስት ዶክተር ጥላሁን ገሠሠ ሥም አደባባይና ሃውልት ለመሥራት የመሰረት ድንጋይ መቀመጡን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ‹‹ቆሜ ልመርቅሽ›› በሚል በሸገር ወዳጅነት ፓርክ የሚደረገው ዝክረ ጥላሁን ኮንሰርት ላዘጋጁ አካላት ምስጋና አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገጻቸው የዝክረ ጥላሁን ገሠሠን ዝግጅት በማስተባበር፣ የተገኘው ገቢ ለ‹‹ገበታ ለሀገር›› እንዲውል ያደረጋችሁ ሁሉ ምስጋናዬ እና አድናቆቴ ይድረሳችሁ ብለዋል።
በተጨማሪም ለተሰበሰበው ከ80 ሚሊየን የሚበልጥ ገንዘብ መዋጮ ያደረጋችሁ ሁሉ የማይደበዝዝ አሻራችሁን በኢትዮጵያ ልማት ላይ አሳርፋችኋል ሲሉ አስፍረዋል።


ቅጽ 2 ቁጥር 122 የካቲት 27 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com