ከመጋቢት እስከ መጋቢት

Views: 84

የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ ታሕሳስ 2012 መጨረሻ ጀምሮ ቫየረሱ ከየት መጣ? ገዳይነቱስ ምን ያህል ነዉ? በግዑዝ ነገሮች ላይስ ምን ያህል ጊዜ ይቆያል? ክትባቱስ መቼ ያጀመር ይሆን? ምን ያክል ገዳይ ነው? መቼ መፍትሄ ይገኝለታል? የሚሉትና ሌሎቸ አነዚህን የመሳሰሉ ጥያቄዎች ለወራት በብዙዎች ዘንድ ተደጋግመው ይነሱ የነበሩ ጉዳዮች ነበሩ።
በሽታው ሲጀምር በትኩሳት ቀጥሎም ደረቅ ሳል ፤ከዚያም ከሳምንት በኋላ የትንፋሽ ማጠርን በማስከተል ህሙማንን በሆስፒታል ውስጥ ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ ድጋፍ እንዲያስፈልጋቸው ሊያደርግ ይችላል።

ከ200 በላይ ክትባቶች
ከአንድ ዓመት በፊት ኮሮናቫይረስን ለመከላከል ይረዳሉ ተብለው ጥናት ሲደረግባቸው የነበሩ ክትባቶች ቁጥር ስምንት ነበር። ባዮሬንደር የተሰኘው ድርጅት እንደሚለው አሁን ከ195 በላይ ክትባቶች በተለያዩ የሂደት ደረጃ ላይ ሲሆኑ 71 ያህሉ ደግሞ በሙከራ ደረጃ ላይ ናቸው። ፀረ-ኮሮና ቫይረስ ክትባቶችን ለማምረት የወጣውን ወጪ፣ ትብብርና ጥናት ያክል ለሌሎች በሽታዎች ይህን የመሰለ ርብርብ አልተደረገም ይላሉ ባለሙያዎች።

በዚህ ጥናት ላይ ሕዝቡ፣ የግል ድርጅቶች፣ አጥኚዎች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ መድኃኒት አምራቾች፣ እንዲሁም መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተሳትፈዋል። አንዳንድ የጥናት ሂደቶች ሳይሰኩ መቅረታቸው እንዳለ ሆኖ ማት ነው።
እስካሁን የዓለም ጤና ድርጅት ፋይዘር/ባዮንቴክ፣ ሞደርና፣ አስታራዜኔካ/ኦክስፎርድ፣ ስፑትኒክ 5 እንዲሁም የቻይናው ሲኖፋርምና ጎል ተብለው የሚጠቀሱ ክትባቶች አጽድቋል። ቢያንስ 20 ተጨማሪ ሌሎች ክትባቶች ደግሞ የሙከራ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
እስራኤል በርካታውን ዜጎቿን በመከተብ ከዓለም ቀዳሚ ናት። እስካሁን ድረስ ባለው መረጃ ከ3.67 በላይ እስራኤላዊያን የፋይዘርን የመጀመሪያ ዙር ክትባት ወስደዋል። ይህ ከአገሪቱ ሕዝብ 40 በመቶውን የሚይዝ ነው። ከ28 በመቶ በላዩ ደግሞ ሁለተኛውን ዙር ክትባት ወስደዋል።

ከ60 ዓመት በላይ ከሆናቸው ዜጎቿ መካከል ደግሞ 80 በመቶው ተከትበዋል። የክትባቶቹ የመጀመሪያ ዙር ውጤት እንደሚያሳየው ክትባቶች እስካሁን ድረስ ባለው ጥናት መሠረት ውጤታማ መሆናቸውን ነው። በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥርም ከጊዜ ጊዜ እየቀነሰ መጥቷል፤ በለተይ ደግሞ ዕድሜያቸውን 60ና ከዚያ በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ።

ሁለቱንም ዙር ክትባት ከወሰዱ 523 ሺህ እስራኤላዊያን መካከል 544 ሰዎች ላይ ብቻ ነው ኮቪድ-19 የተገኘው። እስካሁን ድረስ የተመዘገበ ሞት ግን የለም።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ የክትባቶች ሁሉ ትልቁ ደንቃራ በሳይንስ ቋንቋ አናፊላክሲስ የሚባለው ወይም የክትባቶች ጎንዮሽ ጉዳት ነው። ይህም ምናልባትም ክትባት ከተወሰደ በኋላ ወዲያው የሚከሰት እና እስከሞት ሊያደርስ የሚችል ተጽእኖ ያለው ነው።
ከዚህ አንጻር አሜሪካ ውስጥ ክትባቱ በተሰጠበት የመጀመሪያው ወር ላይ የተሠራ ጥናት እንደሚጠቁመው 17.5 ሚሊየን ክትባቶች ተሰጥዋል። ከእነዚህ የፋይዘርና የሞደርና ክትባቶችን ከወሰዱ ሰዎች መካከል 66ቱ ብቻ የጎንዮሽ ጉዳት እንደ ገጠማቸው ተነግሯል ። ይህ በሚሊዮንኛ ሲሰላ ከአንድ ሚሊዮን ሰው 4 ብቻ ነው ማለት ነው።

ከ66ቱ ሰዎች መካከል 21 ሰዎች ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ ችግር ገጥሟቸው እንደነበር እና በዚህ የጎንዮሽ ጉዳት ምክንያት እስከዛሬ ድረስ የሞተ ሰው አለመኖሩን ጥናቱ አመላክቷል። የዚህ ጥናት ውጤት ለጊዜውም ቢሆን የሚጠቁመው ክትባቶች ከጉዳታቸው ጥቅማቸው በእጅጉ እንደሚያመዝን መሆኑ ነው።

በአለማችን ላይ 313 የሚሆኑ ዜጎች ክትባቱ የተሰጣቸው ሲሆን ከአሜሪካ በተጨማሪ ቻይናም 4 በመቶ የሚሆኑ ዜጎቿን መከተቧን ያስታወቀች ሲሆን የመጀመሪያውን የኮቪድ ፓስፖርትም መስጠት ጀምራለች። ይህም የአገር እና የውጪ ጉዞዎችን በማሳለጥ የቱሪዝም ኢንዱስትሪዋን ከማነቃቃት አንደሚያግዛት ተነግሯል።

በአብዛኞቹ የአውሮፓ አገራት ያሉ በዕድሜ የገፉ ሰዎች አሁን ክትባቱን ካገኙ በኋላ የመያዝ ዕድላቸውና የሞት ቁጥር በእጅጉ እየቀነሰ ነው።
የጤና ሚኒስቴር ዛሬ ቅዳሜ መጋቢት 4 / 2013 በሁሉም ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች ክትባቱ እንደሚሰጥ ታዉቋል። ክትባቱን ለመስጠት የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶች ማከናወኑንም ሚንስቴሩ ገልጿል።በመጀመሪያም ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ማለትም የጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞች፣ እድሜያቸው ከፍ ያሉ እና ተጓዳኝ ህመም ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ክትባቱን እንደሚያገኙ ተጠቁሟል።

ኢትዮጵያ በኮቫክስ ዓለም አቀፍ ጥምረት አማካኝነት 2 .2 ሚሊዮን የመጀመሪያው ዙር የኮቪድ 19 ክትባት ማግኘቷ ይታወሳል። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ወረርሽኙ መከሰቱን በተናገሩ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ክትባቱ መገኘቱ በታሪክ የመጀመሪያ እንደሆነ ይነሳል። በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ክትባት የተገኘለት ወረርሽኝ ወይም በሽታ አይገኝ።

ኮቫክስ የተሰኘው የክትባት አምራች እስከ 2021 ድረስ በትንሹ 2 ቢሊየን የኮቪድ ክትባቶችን አምርቶ ለማሰራጨት እቅድ እንዳለው አስታቀወቋል። ከዚህም መካካል 1.3 ቢሊየን በ እርዳታ ሰጪ ተቋማት የሚሸፈን አንደሚሆን ያለውን ግምት አስቀምጧል።
በአፍሪካ አህጉር በኮቪድ 19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 4 ሚሊዮን ገደማ የደረሰ ሲሆን ቫይረሱን ለመዋጋት በሚደረገው የኮቫክስ ፕሮግራም ንቅናቄ 4 ሚሊዮን 27 ሺ 23 የሚሆኑ ሰዎች ክትባቱን ማግኘታቸው ተገልጿል።
በአፍሪካ በኮቪድ 19 ምክንያት የሟቾች ቁጥር ከ 100ሺ በላይ ሲያሻቅብ 3 ሚሊዮን 512 ሺ 429 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል ተብሏል።

ከአህጉሩ ደቡብ አፍሪካ በቀዳሚነት የተቀመጠችው አገር ስትሆን እስካሁን ድረስ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿ በበሽታው ተይዘዋል። ቁጥራቸው ከ50 ሺ በላይ የሚሆኑትም በዚሁ ወረርሽኝ ሞተውባታል።
ከደቡብ አፍሪካ በመቀጠል ሞሮኮ፣ቱኒዚያ፣ግብጽ፣ኢትዮጵያ እና ናይጀሪያ በከፍተኛ የተጠቂዎችን ቁጥር በመያዝ በቅደም ተከተል ተቀምጠዋል ሲል ኦል አፍሪካ አስነብቧል።
ኢትዮጵያ 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን የመጀመሪያ ዙር የኮቪድ 19 ክትባቶችን ልክ የዛሬ ሳምንት ስትረከብ በመጀመሪያ ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞች፣ ተጓዳኝ ህመም ያለባቸውና በዕድሜ የገፉ የህብረተሰብ ክፍሎች ክትባቱን እንዲያገኙ እንደሚደረግ ተገልጿል።

ሃሰተኛ የኮቪድ 19 ክትባቶች በመሰራጨት
ትክክለኛ ያልሆኑ የኮቪድ 19 ክትባቶች እየተሰራጩ መሆናቸውን ሌላው ስጋት የፈጠረ ጉዳይ እንደሆነ መዘንጋት የለበትም። የዓለም መንግስታት ኬኒያን ጨምሮ ሃሰተኛ የኮቪድ 19 ክትባቶች በመሰራጨት ላይ መሆናቸውን አስመልክቶ አገራት ጥንቃቄ ያደርጉ ዘንድ ጥሪ ማቅረቡ ያታወሳል።

ሃሰተኛ የኮቪድ 19 ክትባቶች በመሰራጨት ላይ መሆናቸውን አስመልክቶ ከደቡብ አፍሪካና ቻይና መረጃዎች እየወጡ ሲገኝ ከጎረቤት ሃገር ኬኒያም እንዲሁ ተመሳሳይ መረጃዎች በስፋት እየወጣ ይገኛል።
ዓለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም ኢንተር ፖል ከሶስት ወራት በፊት አንድ ማስጠንቀቂያ የሰጠ ሲሆን ተቋሙ በወቅቱ እንዳለው ወንጀለኛ ቡድኖች የክትባቱ ስርጭት በመዘግየቱ ምክንያት ሃሰተኛና ጤነኛ ያልሆኑ ክትባቶችን በጥቁር ገበያ ለሽያጭ እያቀረቡ መሆናቸውን ገልጾ ነበር።

ለምሳሌ እንደ ኬንያ ባሉ አገራት ክትባቶቹ ለጥቅም በዋሉባቸው አገራት የአቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር ሲደረግ መቆየቱ ተገልጿል። በደቡብ አፍሪካም በአንድ ከተማ በተደረገ አሰሳ ከ2ሺ 400 በላይ ቁጥር ያላቸው ክትባቶች ተፈብርከው ተገኝተዋል።
ቻይናን ስንመለከት ከአንድ ህገ ወጥ ድርጅት የተመረቱ ከ 3ሺ በላይ ሃሰተኛና ጤነኛ ያልሆኑ ክትባቶች ተገኝተዋል። በዚህም በርካቶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኦል አፍሪካ አስነብቧል።
ኢትዮጵያ በኮቫክስ ፕሮግራም አማካኝነት 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን የአስትራ ዜኒካ ክትባቶችን የተረከበች ሲሆን ፣ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ለሌሎች 19 አፍሪካ አገራት ክትባቱን ማሰራጨቱ ታውቋል።
የኮቪድ ወረርሺኝ ከመከላከል ጎን ለጎን በኮቪድ ለሚያዙ የህብረተሰብ ክፍሎች የህክምና አገልግሎት በተሟላ መልኩ የሚሰጡ የጤና ተቋማት የማደራጀት እና የማዘጋጀት ስራ በጤናው ዘርፍ ሲሰራ መቆየቱ ይታወቃል።
ከተደረጉ ዝግጅቶች ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው በመንግስት እና በግል ተቋማት ደረጃ የሚመረተውን የኦክሲጅን መጠን ማሳደግ፣ ስርጭቱን ወቅታዊ እና ፍትሀዊ ማድረግ እንዲሁም በጤና ተቋማት ደረጃ አጠቃቀሙን ማሻሻል ነው። ከአንድ አመት በፊት እንደ ሀገር የነበረው የኦክሲጅን ማምረት አቅም በእጥፍ ማሳደግ የተቻለ ሲሆን የማሰራጨት አቅም ለማሳደግ ከስድስት ሺህ በላይ የኦክሲጅን ሲሊንደሮች ተገዝተው ተሰራጭተዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በበሽታው የሚያዙ እና ወደ ህክምና ተቋማት የሚገቡ ታካሚዎች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ በመምጣቱ የኦክሲጅን አቅርቦት ላይ ትልቅ ተፅእኖ እያሳደረ ይገኛል። ይህንንም ተጽዕኖ ለማቃለል በሀገራችን ከሚገኙ የኮቪድ ህክምና ተቋማት ውስጥ ብዙ የታካሚዎች አልጋ ያለው የሚሊኒየም ኮቪድ ህክምና ማዕከል ብዙ ኦክሲጂን የሚጠቀም በመሆኑ እና ታካሚዎች በኦክሲጅን አቅርቦት ማነስ ችግር ላይ እንዳይወድቁ የራሱ የሆነ የኦክሲጅን ማምረቻ ማሽን ተከላ ተከናውኖዋል። የዚህ ማሽን ተከላ እንዲሳካ አስተዋጽዎ ያደረጉትን የቢልና ሜልንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በገንዘብ ልገሳ፣ የግዢ ሂደቱን ያስተባበረውን ክሊንተን ሄልዝ አክሰስ ኢኒሼቲቭ እንዲሁም መሳሪያውን ያቀረበውን ሜድስታር ሄልዝ መሆኑ ታውቋል።
የኮቪድ19ን አሳሳቢነት አሁንም በመገንዘብ ህብረተሰባችን የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ በመጠቀም፣ አላስፈላጊ መሰባሰቦችን በማስወገድ እና ሲንቀሳቀሱ ርቀትን በመጠበቅ የበሽታውን ስርጭት መግታት ይኖርበታል።


ቅጽ 2 ቁጥር 123 መጋቢት 3 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com