መራጮች በመራጭነት ለመመዝገብ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች
አንድ ሰው በመራጭነት ለመመዝገብ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅበታል፡፡
- ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ መሆን ይገባዋል
- ዕድሜው 18 እና ከዚያ በላይ መሆን አለበት
- በምርጫ ክልሉ ቢያንስ ስድስት ወር የኖረ መሆን ይገባዋል
- ቢሆንም የአእምሮ ሕመም ያለባቸው ሰዎች እንዲሁም የመምረጥ መብታቸው በሕግ የታገደባቸው ሰዎች ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ቢያሟሉም እንኳን በመራጭነት መመዝገብ አይችሉም
- አንድ መራጭ በአንድ ምርጫ ጣብያ ከአንድ ጊዜ በላይ ወይም በሌላ ምርጫ ጣብያ በድጋሚ መመዝገብ አይችልም
- የመራጮች ምዝገባ እንደተጠናቀቀም የመራጮች መዝገብ በምርጫ ጣብያው ቅጥር ግቢ ውስጥ ለ10 ቀናት ይፋ ወጥቶ ሕዝብ በግልፅ እንዲያየው መደረግ አለበት፡፡
ምንጭ፡- የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
ቅጽ 2 ቁጥር 123 መጋቢት 3 2013