‹‹ሀገር ስታምጥ›› መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Views: 41

በአሁን ወቅት በማረሚያ ቤት በምትገኘው አስቴር ስዩም የተዘጋጀ ‹ሀገር ስታምጥ› የተሰኘ መጽሐፍ በዛሬው እለት/ቅዳሜ መጋቢት 18 ቀን 2013 ከቀኑ 8 ሰዓት በኢትዮጵያ ሆቴል ተመርቆ ለንባብ ይበቃል።
መጽሐፉ የደራሲዋን የሕይወት ታሪክ የሚዳስስ ሲሆን፣ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ያለውን የፍትህ ስርዓትና በእስር ቤት ያለውን ችግር የሚዳስስ ነው ተብሏል።
ከዘጠኝ ወራት ገደማ በፊት ለእስር የተዳረገችው አስቴር ስዩም፣ ቦ317 ገጾች ያዘጋጀችውን የዚህን መጽሐፍ ከፊል ክፍል አስቀድማ የጀመረችው እንደነበርና፣ ቀሪውን ክፍል ደግሞ አሁን በምትገኝበት በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሆና ያጠናቀቀችው እንደሆነ ባለቤቷ በለጠ ጌትነት ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
በዛሬው እለት በሚኖረው የመጽሐፉ ምርቃት መሰናዶ ላይ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ፕሬዝዳንት ማሙሸት አማረ፣ የባልደራስ የጽሕፈት ቤት ኃላፊ ገለታው ዘለቀ፣ መስከረም አበራ፣ አስቴር በዳኔ፣ ሲሳይ መንግሥቴ (ዶ/ር) እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ተብሏል።
የኹለት ልጆች እናት የሆነችው አስቴር ስዩም ከዚህ ቀደም በነበረው የኢሕአዴግ ስርዓት አራት ዓመታትን በእስር አሳልፋለች። ከዘጠኝ ወራት ገደማ አስቀድሞ አስቴር ስዩምን ጨምሮ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀ መንበር እስክንድር ነጋ እና የፓርቲው አመራር አባላት ስንታየሁ ቸኮል በሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት ጋር ተያይዞ ግጭት በመቀስቀስ ተጠርጥረው በፖሊስ ተይዘው አሁንም በእስር ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።


ቅጽ 3 ቁጥር 125 መጋቢት 18 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com