‹‹እቅድ ብቻውን ስኬት አይደለም››

Views: 108

የትራንስፖርት ሚኒስቴር መጋቢት 15-16 በስካይ ላይት ሆቴል የትራንስፖርት ኢንቨስትመንት ጉባዔ አካሂዷል፡፡ ኢትዮጵያም <በ2022 አስተማማኝ፣ የተቀናጀ ዘመናዊና ደኅንነቱ የተረጋገጠ የትራንስፖርትና የሎጀስቲክስ አገልግሎት ለሁሉም ኅብረተሰብ ተደራሽ በማድረግ የኢትዮጵያን ብልጽግና ማረጋገጥ> የሚል ራዕይ በመሰነቅ የዘርፉን የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ በማጸደቅ ወደ ሥራ መገባቱን ሚንስትሯ ዳግማዊት ሞገስ ገልጸዋል።
ዕቅዱን ለማሳካት የግሉንም ዘርፍ በስፋት ለማሳተፍ በብሔራዊ የትራንስፖርት ፖሊሲና ሌሎች ስትራቴጂዎች በግልጽ መቀመጡ ተገልጿል ።
በጉባዔው መክፈቻ ላይ የተገኙት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ “ምንም ያህል በግብርናም ሆነ በማንኛውም የኢኮኖሚ ዘርፍ ላይ እንደ አገር ስኬታማ ብንሆንም የትራንስፖርትና የሎጀስቲክስ ስኬት ካልታከለበት ውጤታማ አንሆንም” ብለዋል።
‹እቅድ ብቻውን ስኬት አይደለም› ያሉት ፕሬዝዳንቷ፤ ውጤት እንዲመጣ ሁሉም አካል የራሱን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል
የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ላይ የትራንስፖርት ዘርፉን በማዘመን፣ አገልግሎቱን ማስፋፋትና የዘርፉን አቅም ማጎልበት ላይ ትኩረት በመሰጠቱ የግሉ ባለሀብት ይህንን ዕድል እንዲጠቀምበት አሳስበዋል፡፡


ቅጽ 3 ቁጥር 125 መጋቢት 18 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com