10 ከፍተኛ የሴቶች ጥቃት የሚከሰትባቸው የዓለማችን ክፍለ አህጉራት

Views: 139

ምንጭ፡-(Global Gender Gap)

የዓለም ኢኮኖሚክ መድረክ (The World Economic Forum’s) በ2020 የዓለም አቀፍ የሥርዓተ-ፆታ ክፍተትሪፖርቱ እንዳመለከተው በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ከአንድ አምስተኛ እስከ ግማሽ ያህል የሚሆኑ ሴቶች ከወንድ አጋሮቻቸው አካላዊ ወይም ወሲባዊ ጥቃት እንደሚገጥማቸው አስታውቋል።
እንደ ሪፖርቱም ከሆነ በመካከለኛው ምስራቅ እና በሰሜን አፍሪካ ውስጥ 45 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ጉዳት የደረሰባቸው በመሆናቸው ከፍተኛውን ደረጃ ይይዛሉ።
ችግሩ ግን በምስራቅ እና በሰሜን አፍሪካ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም የቀጠለ እንደሆነም ተገልጿል። በሰሜን አሜሪካ ውስጥ የጥቃት መጠኑ 32 በመቶ ሲሆን በምዕራብ አውሮፓ ደግሞ 22% እንዲሁም በእንግሊዝ ውስጥ አንድ ወንድ በአገሪቱ ውስጥ በየሦስት ቀኑ አንድ ሴትን እንደሚገድል በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው የዳሰሳ ጥናት (Femicide Census) ዘገባ ያሳያል። ይህ ቁጥርም ለባለፉት 10 ዓመታት ያልተለወጠ አኃዛዊ መረጃ እንደሆነም ተገልጿል።


ቅጽ 3 ቁጥር 126 መጋቢት 25 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com