ባልደራስ የምርጫ ማኒፌስቶውን አስተዋወቀ

Views: 93

“አዲስ አበባን ማዳን ኢትዮጵያን ማዳን ነው “ በሚል መሪ ሀሳብ ማኒፌስቶውን መጋቢት 23/2013 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዋወቀ።
ፓርቲው በማኒፌስቶው እንደገለፀው አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግሥት ሕወሃትን ቢያስወግድም የዜጎች ሞት እና ስደት ግን ተጠናክሮ ቀጥሏል ብሏል። አዲስ አበባን በተመለከተ ያለውን “የህገወጥነት ፖለቲካ” እታገላለሁ ነው ያለው። “አዲስ አበባ ራስ ገዝ እንድትሆን እና በራሷ ልጆች እንድትመራም “ ፓርቲው እንደሚሠራ ገልጿል።
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ በማንነታቸው ተለይተው ለተገደሉት አማራዎች መንግሥት “ተጠያቂ ነው” ብሏል። መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት መጠበቅ ቁልፍ ተግባሩ ቢሆንም “በተግባር” አልተገለጸም ብሏል። ፓርቲው ከሕዝብ ጋር ሆኖ ድርጊቱን እስከመጨረሻው እንደሚታገለውም ገልጿል።
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ምርጫውን በአብላጫ ድምፅ ካሸነፈ በመጀመሪያ ሕገ መንግስቱ እንዲለወጥ ሕገ መንግስት አርቃቂ ኮሚሽን እንደሚያቋቁም በማኒፌስቶው ገልጿል።


ቅጽ 3 ቁጥር 126 መጋቢት 25 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com