ምርጫ ቦርድ በእስር ላይ ያሉ የባልደራስ አመራሮች በዕጩነት መመዝገብ በፍርድ ሂደታቸው ላይ ተጽእኖ ያሳድራል አለ

Views: 115

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) በከፍተኛ ፍርድ ቤት ላቀረበው ክስ ባሳለፍነው ሰኞ መጋቢት 20/2013 በችሎት ፊት ምላሽ ሰጠ። ቦርዱ ለአንደኛ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት በሰጠው ምላሽ በሕግ ከለላ ስር ያሉት የባልደራስ ዕጩዎች ለምርጫ መመዝገብ የማይችሉባቸውን ኹለት ምክንያቶች አስረድቷል።
የባልደራስ አመራሮቹ ለምርጫ በዕጩነት ቢመዘገቡ በቀጥታ ያለመከሰስ መብት ስለሚኖራቸው፤ በሌላ ችሎት እየታየ ባለው የተከሳሾቹ የፍርድ ክርክር ሂደት ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል ሲል ቦርዱ ባሳለፍነው ሰኞ በዋለው ችሎት መግለጹን የባልደራስ ፓርቲ ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። ምርጫ ቦርድ አመራሮቹ ለምርጫ እንዳይመዘገቡ “የኢትዮጵያ የምርጫ ሕግ እና የምርጫ ቦርድ መመሪያ ይከለክላል” በሚል ተጨማሪ ምክንያት ማቅረቡንም አክለዋል።
ባልደራስ በእስር ላይ የሚገኙትን የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች እነ አስክንድር ነጋ በምርጫ እንዲወዳደሩ እጩ አድርጎ ለማቅረብ ለምርጫ ቦርድ ያቀረበው ጥያቄ በቦርዱ ውድቅ እንደተደረገበት የሚታወስ ነው።


ቅጽ 3 ቁጥር 126 መጋቢት 25 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com