መንግሥት ለፖለቲካ ፓርቲዎች የመደበው 98 ሚሊዮን ብር ሊከፋፍል ነው

Views: 129

መንግሥት ለፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲከፋፈል በዚህ ዓመት የመደበው 98 ሚሊዮን ብር ውስጥ፤ የተወሰነው መጠን በሚቀጥለው ሳምንት ለፖለቲካ ፓርቲዎች መከፋፈል ሊጀመር ነው። ለፓርቲዎች የሚሰጠው ገንዘብ ለሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በእኩልነት እንዲከፋፈል በቀመር አማካኝነት የተደለደለ ነው ተብሏል።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተዘጋጀው የክፍፍል ቀመር መሰረት መንግስት ለፓርቲዎች ከሚመድበው ገንዘብ ውስጥ 25 በመቶ ያህሉ፤ በቦርዱ ዕውቅና ተሰጥቷቸው ለሚንቀሳቀሱ ለሁሉም ፖለቲካ ፓርቲዎች በእኩልነት ይከፋፈላል። የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በነበራቸው ውይይት ላይ እንደተናገሩት፣ የገንዘብ ድጋፍ ከምርጫ ጋር ብቻ የተገናኘ እንዳልሆነ ጠቁመዋል።
“መንግሥት ፓርቲዎች የህዝብ ፍላጎት መሰረት እያደረጉ፣ ወደ አማራጭና ወደ ፖሊሲ ለሚቀይሩ ፓርቲዎች ሁልጊዜም ድጋፍ የማድረግ ግዴታ አለበት” ብለዋል ሰብሳቢዋ። “በእኩልነት መርህ ላይ ተመስርቶ በሚከፋፈለው ገንዘብ ላይ ህጋዊ ዕውቅና ያላቸው ፓርቲዎች በሙሉ ተካፋይ ይሆኑበታል” ሲሉም አክለዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 126 መጋቢት 25 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com