10ቱ ከፍተኛ ሰላምና ነፃነት ያላቸው፣ ለሥራ ምቹ የሆኑ አገራት

Views: 456

ምንጭ፡-ግሎባል ፋይናንስ (2020)

ግሎባል ፋይናንስ በ2020 ነሐሴ ወር ባወጣው ዘገባ፣ በዓለም ላይ ሀብት ለማፍራት የሚቻልባቸው እንዲሁም ሰላም የሰፈነባቸውና ነጻነት የሚገኝባቸው አገራት በማለት በዐሰርቱ ዝርዝር ለይቶ አስቀምጧል።
የአንድ አገር የእድገት ሁነኛ ምንጭ የሰላም ሁኔታ መጠበቁ እንደሆነ ይታመናል። እናም አንድ ሰው ካለበት አገር ወደ ሌላ አገር ለሥራም ይሁን ለመኖር እንቅሰቃሴ ሲያደርግ ቀድሞ የሚታየው የግለሰብ ጥበቃ (ለችግር ተጋላጭ ነው ወይ) የሚለው ሲሆን፣ ቀጣዩ ደግሞ ሰላም ነው ወይስ ሁከት አለው የሚለው ነው።
ከዛም ባለፈ የተፈጥሮ አደጋዎች የመከሰት እድል ይቃኛል። እነዚህን ሁሉ ነጥቦች መሠረት አድርጎና አካትቶ ግሎባል ፋይናንስ እንዳወጣው ሪፖርት ለአደጋ ተጋላጭ (ሰላምና መረጋጋት ያለባቸው አገራት) ብሎ ካወጣቸው ውስጥ አይስላንድ አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
ሲውዘርላንድ፣ ፊንላንድ እና ፖርቹጋል ደግሞ ከኹለተኛ እስከ አራተኛ ደረጃ የያዙ ሲሆን፣ አውስትራሊያ፣ ኖርዌይ ኳታር ከአምስት እስከ ሰባተኛ፣ በመጨረሻም ሲንጋፖር፣ ዴንማርክ እና ኒውዘርላንድ ከስምንት እስከ ዐስረኛ ደረጃ ተቀምጠዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 127 ሚያዚያ 2 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com