ግጭት እና ኮረና

Views: 10

በአፍሪካ አገራት እየተባባሱ የመጡ ግጭቶች የኮሮና ቫይረስን እንዲስፋፋ ምክንያት እየሆኑ ነው ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል በያዝነው ሳምንት ባወጣው ሪፖርት ገልጿል።በተለይ ከሰሀራ በታች ባሉ አገራት በታጠቁ ቡድኖች መካከል የሚደረጉ ግጭቶች ለኮሮና ቫይረስ ስርጭት መስፋፋትን የጎላ ሚና እንዲኖራቸው አድርጓል ብሏል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት እ.ኤ.አ. 2020/21 የአለም የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ከሰሃራ በታች ባሉ አፍሪካ ውስጥ 35 ቱን ጨምሮ 149 አገሮችን የሚሸፍን ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ በ 202 የሰብአዊ መብቶች አዝማሚያዎችን አጠቃላይ ትንታኔ ይሰጣል ። ድርጅቱ ባወጣው ዘገባ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አካባቢዎች በመንግስታቶቹ እና በታጠቁ ቡድኖች መካከል ግጭት ተባብሶ ቀጥሏል ያለ ሲሆን፣ በማሳያነትም በደቡባዊ አፍሪካ አካባቢ በምትገኘው በሞዛንቢክ ካቦ ዴልጋዶ አወራጃ እንዲሁም በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል በሚገኘው በትግራይ ክልል ግጭቶች መከሰታቸው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት አሁን ካለው በላይ በባሰ ሁኔታ እንዲባባስ እድል እየፈጠረ ነው ብሏል።

የምስራቅና የደቡብ አፍሪካ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዳይሬክተር ዲፕሮሴ ሙቼና የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ ግጭት መከሰቱን ተከትሎ የቫይረሱ ስርጭት ያባብሰዋል ብሏል ።
ሪፖርቱ አክሎም ኮሮና ቫይረስ መባባሱ ብሎም ግጭቶች መኖራቸው ደግሞ በብዙ አገራት ውስጥ ቀድሞውኑ አስጊ የነበረውን የስደተኞች እና ተገን ጠያቂዎች አያያዝ ላይ ችግር ከመፍጠሩም ባሻገር አስፈላጊ አቅርቦቶች ከድንበር አካባቢ ለማጓጓዝ መዘግየት ያጋጥማል ሲል ድርጅቱ ተናግሯል።

ከባድ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ከኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ባለፈ ፆታዊ ጥቃቶችም ጨምረዋል ብሏል አምነስቲ በሪፖርቱ ። COVID-19 በብዙ አገሮች ውስጥ ቀድሞውኑ የነበረውን የስደተኞች ፣ የጥገኝነት ጠያቂዎች እና ስደተኞች ሁኔታ ያባባሰ ፣ ለስደተኞች አስፈላጊ አቅርቦቶችን እንዲቋረጡ ከማድረግ በተጨማሪ የድንበር ቁጥጥሮችን ጫና መፍጠሩን አስታውቋል።

ለምሳሌ በአፍሪካ ትልቁ ስደተኞችን የሚያስተናግድ 1.4 ሚሊዮን ስደተኞችን የያዘች ድንገተኛ ወረርሽኝ በተነሳበት ወቅት ድንበሯን ወዲያውኑ በመዝጋት ወደ አገሩ ለመግባት ለሚሞክሩ ስደተኞች እና ጥገኝነት ፈላጊዎች መከልከሏን አስታውሷል ። በዚህ ምክንያት ከ 10,000 በላይ ሰዎች ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (ዲ.ኮ.) ጋር በሚያዋስናት ድንበር እንዳይገቡ ተሰናክለው ነበር።

ሪፖርቱ በእንቅስቃሴዎች ላይ ገደብ መጣሉን ተከትሎ የሴቶችን የቤት ውስጥ ጥቃት ላይ ከፍተኛ ጭማሪም እንዳሳየ ገልጿል ። ለአብነትም በደቡብ አፍሪካ እስከ ሰኔ አጋማሽ ድረስ 21 ሴቶች እንዲሁም በናይጄሪያ በ COVID-19 እገዳ ወቅት ከ 3,600 በላይ አስገድዶ መድፈር መመዝግቡን አትቷል ።

በአለም ዙሪያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሚገድላቸው ሰዎች ብዛት እና ምጣኔው በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ነው እንደሆነ እና ወረርሽኙ የገደላቸው ሰዎች ብዛት ከ3 ሚሊዮን በላይ መድረሱ ታውቋል። አንደ ሬውተርስ ዘገባ እስከ አሁን ድረስ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ 2 ሚሊዮን ሰዎች ለመግደል የ1 አመት ጊዜ ሲጠይቀው ሌሎች 1 ሚሊዮን ሰዎች የሞቱት ደግሞ በ3 ወራት ጊዜ እንደሆነ በመረጃው ተጠቅሷል።

በእለታዊ የሞት ብዛት ብራዚል ቀዳሚዋ አገር ነች ተብሏል። በአገሪቱ የፅኑ ህሙማን መከታተያ የሆስፒታል ክፍሎች እየሞሉ መሆኑ በመረጃው ተነስቷል። በሕንድ ደግሞ በየእለቱ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ብዛት የ100,000 ወሰንን ማለፍ ከጀመረ ሰነባብቷል።
በአሜሪካ ወረርሽኙ የገደላቸው ሰዎች ብዛት 555,000 ደርሷል። በመላው አውሮፓ ደግሞ በኮሮና ቫይረስ የሞቱት ሰዎች ብዛት 1.1 ሚሊዮን እንደሆነ በመረጃው ተነስቷል።
በአፍሪካ አህጉር እየተባባሱ የመጡት ግጭቶች እና ጦርነቶች ለወረርሽኙ ሥርጭት ማደግ



ቅጽ 3 ቁጥር 127 ሚያዚያ 2 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com