የባንኮች መነሻ ካፒታል ከ500 ሚሊየን ብር ወደ 5 ቢሊየን ብር ሊያድግ ነው ተባለ

Views: 422

በብሄራዊ ባንክ የባንክ ሱፐርቪዥን ዳይሬክተር ፍሬዘር አያኔው ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት ባንኮች ለምስረታ የሚያስፈልጋቸው ካፒታል ወደ 5 ቢሊየን እንዲያሳድጉ የሚጠይቅ መመሪያ ተዘጋጅቶ ከዛሬ መጋቢት 6 ጀምሮ ለባንኮች እየተላከ መሆኑን ነግረውናል፡፡

ባንኮች የካፒታል አቅማቸው የተጠናከረ እና የዳበረ እንዲሁም ተወደዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል የተሻሻለው ይህ መመሪያ ለነባር ባንኮች እስከ 5 ዓመት እና ለአዳዲስ ባንኮች እስከ 7 ዓመት ጊዜ መሰጠቱን ፍሬዘር ተናግረዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com