ኢትዮ ቴሌኮም በ8100 የፅሑፍ መልዕክት የሰበሰበውን 122.5 ሚሊዮን ብር ለሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፅሕፈት ቤት አስረከበ

Views: 131

ካለፈው ዓመት የካቲት ወር ጀምሮ የተካሄደው የሦስተኛ ዙር በ8100 አጭር የፅሑፍ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ 1.3 ሚሊዮን ሰዎች መሳተፋቸውን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ተናግረዋል። ከስምንት ዓመት በፊት በተካሄደው የመጀመሪያ ዙር የ8100 ገቢ ማሰባሰቢያው 80.3 ሚሊዮን ብር እንዲሁም በኹለተኛ ዘር 49.3 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡንም አስታውሰዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም በድምሩ በሦስት ዙሮች 252 ሚሊዮን ብር ለፅሕፈት ቤቱ አስረክቧል። በርክክብ መርሃ ግብሩ የተገኙት የማስተባበሪያ ፅሕፈት ቤቱ ኃላፊ አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) በበኩላቸው ለተደረገው የገቢ ማሰባሰብ ሥራና አስተዋፅኦ ላደረጉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በቀጣይም ዜጎች በ8100 የሚያደርጉትን አስተዋፅኦ እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እንዲሁም ማስተባበሪያ ፅሕፈት ቤቱ 122 467 676 ቼክ ተረክበዋል። 20 ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉ ግለሰቦች እንዲሁም ተቋማት ሥማቸው ተጠቅሶ ምስጋና ተቸረዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com