10ምግብ አባካኝ አገራት

Views: 67

ምንጭ፡-የተባበሩት መንግሥታት የኢንቫይሮመንት ፕሮግራም – 2021

የተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ፕሮግራም (UNEP) በ2021 ባወጣው የሚባክን ምግብን የተመለከተ ዘገባ መሠረት፣ በዓለማችን በየዓመቱ በድምሩ 931 ሚሊዮን ቶን ምግብ ይባክናል።
ከዚህም 61 በመቶ ከቤት ውስጥ የሚነሳ ሲሆን 26 በመቶ ከምግብ አቅራቢ ተቋማት እንዲሁም 13 በመቶ በግብዓት ደረጃ ሳለ የሚባክን ነው ይላል፤ ዘገባው።
ይህ የምግብ ብክነት መጠጥን እንዲሁም በምግብ አቅርቦት ሂደት ውስጥ የሚጣሉትን የሚጨምር ነው። እነዚህም መዳረሻቸው የቆሻሻ መጣያ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ አልያም ለአፈር ማዳበሪያነት ይውሉ ዘንድ መሬት ላይ ነው።
በዘገባው መሠረት በዚህ መልክ የሚባክኑ ምግቦች አማካይ ከፍተኛ ሆኖ የሚገኘው በእስያ ነው። ይህም 110 ኪሎግራም ነው። አፍሪካ በ108 ኪሎግራም ኹለተኛ፣ እንዲሁም ደቡብ አውሮፓ በ90 ኪሎግራም ሦስተኛ ናቸው። ከአፍሪካ ናይጄሪያ ምግብ በማባከን በቀዳሚነት ስትገኝ፣ ኢትዮጵያ ትከተላለች። ግብጽ በ9.1 ሚሊዮን ቶን ሦስተኛ ምግብ አባካኝ ሆና ትከተላለች።


ቅጽ 3 ቁጥር 129 ሚያዚያ 16 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com