በህገወጥ እርድ ምክንያት የአዲስ አበባባ ከተማ አስተዳደር ከአንድ ቢሊዬን ብር በላይ እንደሚያጣ ተገለፀ

Views: 87

መንግሥት በህገወጥ እርድ ምክንያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደረጃ በአመት ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚያጣ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት እና የከተማ አስተዳደር አርሶ አደርና ግብርና ልማት ኮሚሽን በጋራ በሰጡት መግለጫ ለአዲስ ማለዳ አስታወቁ።
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ባለፈዉ ለገና በአል እስከ 3500 ሺ የሚጠጉ እንስሳትን ለእርድ ማቅረቡ ይታወሳል። የፊታችን እሁድ ለሚከበረዉ የፋሲካ በአል ደግሞ ከ1500-2000 የሚጠጉ በግና ፍየሎች እና እንዲሁም እስከ 3500 የሚጠጉ በሬዎችን በአጠቃላ ከ4500 እስከ 5000ሺህ የሚጠጉ እንሰሳት ለእርድ እንደሚጠጉ ተገልጻል። ከዚህም ጋር አያይዘዉ የአንድ በግ የእርድ ዋጋ 100 ብር ሲሆን የአንድ በሬ የእርድ ዋጋ ደግሞ 800 ብር እንደሚሆን አዲስ አበባ ቄራዎች ዲርጅት የህዝብ ግንኙነት ሀላፊዉ አታክልቲ አስታዉቀዋል።

ከዚህ በፊት የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በብዛት የእርድ አገልግሎት ለሉካንዳ ቤቶች ይሰጥ እንደነበር ይታወቃል ። በአሉን ምክንያት በማድረግ ግለሰቦች አንድም በግ ቢሆን ይዞ ለሚመጣ የእርድ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን ድረጂቱ አስታዉቋል።
ድርጅቱ ከዚህ በፊት አጋጥሞት የነበረዉን የስርጭት መዘግየትን ለመቅረፍ ቆመዉ የነበሩ መኪኖችን በመጨመር በበቂ ሁኔታ ዝግጅት ማድረጋቸዉን አታክልቲ ገልጸዋል። ህብረተሰቡ ወደ አዲስ አበባ ቄራዎች ወይም ሌሎች ቄራዎች በመሄድ ንጽህናዉን የእርድ አገልግሎትም ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጻል።

የፋሲካንና የለመዳንን በአል ተከትሎ በከተማችን ዉስጥም ሰፊ ህገ-ወጥ እርድ የከናወናባቸዉ ቦታዎች ብለን ባጠናነዉ ጥናት መሰረት የቆሻሻ መጣያ ቦታዎች፣ በሆቴሎች ጀርባ፣ትላልቅ ግቢ ባላቸዉ የግለሰብ ቤቶች፣ በወንዞች አካባቢ እና የቁም እንሰሳት ማደሪያ የሆኑ በረት ዉስጥ እንደሚከናወን አስታዉቀዉ ይህም ስጋ ለሉካንዳ ቤቶች፣ ለሆቴሎች፣ለሱፐር ማርኬቶችና ለግለሰብ ቤቶች እንደሚቀርቡ የከተማ አስተዳደር አደርና ግብርና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅርተ ገልጸዋል።

ከዘረዘሩዋቸዉ ጉዳቶች መካከል ከእንስሳት ወደ ሰዉ የሚተላለፉ፣ህብረተሰቡን ጤና በጉዳት፣በዘርፉ ህጋዊ ሆነዉ የሚሰሩ ተቋማትን ለኪሳራ ይዳርጋል፣ በሽታ መኖር፣ በዛገና የስጋ መመረዝ፣ ጤናማና አምራች ዜጋ እንዳናፍራ ችግር መፍጠር ፣የአካባቢዎች በመጥፎ ጠረን መመረዝ እና የአካባቢ መቆሸሽ ፣የኮሮና ቫይረስ መመስፋፋትና መንግስት ማግኘት የነበረበትን ገቢ እንዳያገኝ እንደሚደርግ አስታዉቀዋል።

ሕገወጥ እርድ ህብረተሰቡን በሽታ ላይ ከመጣል ባሻገር ከሚታረዱት እንስሳዎች የሚገኘዉን ተረፈ ምርቶች እንደ ቆዳና ሌጦ፣ ሽንፍላ፣እና የመሳሰሉት ወደ ዉጪ ተልከዉ ለአገር መግባት የነበረበትን የዉጪ ምንዛሬ ማሳጣትና በዚህ ዘርፍ ህጋዊ ሆነዉ በሚሰሩ ነጋዴዎችም ላይ የሚፈጥረዉ ጫና እና በተለይም አሁን ላይ ደግሞ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለማስፋፋት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረዉ የከተማዉ ኗሪ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኮሚሽነር ፍቅርተ አሳስበዋል።

በህገ ወጥ እርድ ላይ ለሚሳተፉ ግለሰቦችም ሆኑ ተቋማት ኮሚሽነሩ ከተለያዩ ከሚመለከታቸዉ ቋማት ጋር በመናበብ አስፈላጊዉን እርምጃ እንደሚጥል አስታዉቀዋል። ኮሚሽነሩ ከአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ጋር በመሆን ህጉን ተላልፈዉ ለሚገኙ ግለሰብም ሆኑ ተቋማት በገንዘብ15-20ሺ ብር፣ከሁለት ወር እስከ ሶስት ወር ድረስ የእስራት ቅጣት እና የፈጸሙት ህገወጥ ድርጊት እስኪጣራ ድረስ ድርጅቱ እንደሚታሸግ አስታዉቀዋል። ህብረተሰቡም እረሱን ከህገወጥ እርድ እንዲጠብቅና እንዲከላከል አሳስበዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 130 ሚያዚያ 23 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com