የእለት ዜና

የኢትዮጵያ የውጭ አገር የስራ ስምሪት ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዚያ 28/2013 ባካሄደው 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ስብሰባው የውጭ አገር የስራ ስምሪት ረቂቅ አዋጅን አዋጅ ቁጥር 1246/2013 ሆኖ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
ረቂቅ አዋጁ አዋጅ ቁጥር 923/2008 ለማሻሻልና በስራ ላይ ባለው አዋጅ ያልተሸፈኑ አዳዲስ ድንጋጌዎችን ያካተተ እንዲሁም በአፈጻጸሙ ዙሪያ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ እንደሆነ ተገልጿል።
ከምክር ቤቱ ከተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ከሆነ ረቂቅ አዋጁ የዜጎችን መብት ፣ ደህንነትና ጥቅም በተሻለ መልኩ ሊያስጠብቅ የሚችል መሆኑን ፣ በነባሩ አዋጅ በአፈጻጸም ጉድለት የታየባቸው ድንጋጌዎች ላይ ማስተካከያ መደረጉ ፣ እየሰፋ የመጣውን የውጭ አገር የስራ ስምሪት በተገቢውና በብቃት ማስፈጸም የሚያስችል እንደሆነ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሴቶች ፣ ወጣቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አበባ ዮሴፍ ገልጸዋል ።


ቅጽ 3 ቁጥር 131 ሚያዚያ 30 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!