ፍለተርዌቭ ገንዘብ የማስተላልፍ አገልግሎትን ለማመቻቸት ከዳሸን ባንክና ከሞኔታ ቴክኖሎጂስ ጋር አጋርነትን መሰረተ

Views: 198

በአፍሪካ የክፍያ ቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን እየመራ የሚገኘው ፍለተርዌቭ ዛሬ በኢትዮጵያ ታላቁ ከሆነው የዲጂታል ዋሌት መገልገያ አሞሌ ጋር አጋርነት መመስረቱን አስታወቀ። ይህም አሞሌን በመጠቀም በአሞሌ ዋሌት፣ በባንክ ሂሳቦች እንዲሁም ከ2500 በላይ ባሉ የገንዘብ ማውጫ ቦታዎች ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ እንዲተላለፍ ያስችላል ተብሏል።
አሞሌ ተጠቃሚዎቹ ዲጂታል እቃዎችንና አገልግሎቶችን እንዲጠቀሙና በቀላሉ ዋና ዋና ክፍያዎችን ባሉበት ሆነው እንዲፈፅሙ ያመቻቻል። ከፍለተርዌቭ ጋር የተመሰረተው አጋርነት በዓመት ወደ ኢትዮጵያ ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ለሚልኩ ከ8 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች የገንዘብ ማስተላለፍ ሒደቱን በማቅለል የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ይደግፋል። አለማቀፍ ገንዘብ አስተላላፊዎች፣ ፍለተርዌቭን የሚጠቀሙ የንግድ ተቋማት እንዲሁም የፍለተርዌቭ ባርተር አገልግሎት ተጠቃሚዎች በዚህ አጋርነት ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ መላክ ይችላሉ።
አሁን በኢትዮጵያ ያለው የገንዘብ ማስተላለፍ ሒደት ለዲያስፖራው ማህበረሰብ ውድ ከመሆኑ በተጨማሪ አሰልቺ የወረቀት ስራውን እና የሚከሰቱ መዘግየቶችትን ተከትሎ አስቸጋሪ እና ብዙ ጊዜ የሚወስድ እንደሆነምተመላክቷል። ይሄ አጋርነት ያለምንም ክፍያ ወዲያውኑ ገንዘብን በፈለጉበት ቦታ እና ጊዜ መቆጣጠር ወይም ማየት በሚችሉበት መልኩ ማስተላለፍ እንዲችሉ በማድረግ ይህንን ችግር ይቀርፋል ተብሏል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com