የእለት ዜና

በዘጠኝ ወር ውስጥ 2 ሺሕ 95 አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች መቋቋማቸው ተገለጸ

በዘጠኝ ወር ውስጥ 2 ሺህ 95 አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን በማቋቋም ለ22 ሺህ 774 ዜጎች የሥራ እድል መፈጠሩን የፌዴራል አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ማስፋፊያ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍሬሕይወት ወ/ማሪያም ገልጸዋል። በተጨማሪም 12 ሺህ 21 ነባር ኢንዱስትሪዎችን በማጠናከር ለ38 ሺህ 211 ሰዎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ከተያዘው እቅድ አንፃር ውጤታማ ሥራ መሰራቱን ተናግረዋል።
ባለፉት 9 ወራት ከ8 ሺህ በላይ ኢንዱስትሪዎች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ያገኙ ሲሆን ለ1,643 ኢንዱስትሪዎች ደግሞ የግብዓት አቅርቦት ትስስር ተፈጥሮላቸዋል።
የኢንዱስትሪዎችን የፋይናንስ አቅርቦት ለማሳደግ በተሰራው ስራ ለ638 ኢንዱስትሪዎች የ891.8 ሚሊዮን ብር የስራ ማስኬጃ ብድር የተመቻቸ ሲሆን፣ ለ774 ኢንዱስትሪዎች ደግሞ የ330.8 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው የካፒታል ዕቃ ማቅረብ ተችሏል።
የገበያ ትስስርን በተመለከተም በየደረጃው በተዘጋጁ 11 ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ 455 ኢንዱስትሪዎች እንዲሳተፉ በማድረግ የ5 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የገበያ ትስስር መፍጠር ተችሏል።
በተያያዘም124 የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች 6.37 ሚሊዮን ኪ.ግ. ያላቸውን የተለያዩ የማኑፋክቸሪንግ ምርት ውጤቶችን ወደ ውጭ አገር ገበያ በመላክ የ15 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል ያሉት ወ/ሮ ፍሬሕይወት፣ ከዚህ በተጨማሪም ለ7,221 ኢንዱስትሪዎች የአገር ውስጥ የገበያ ትስስር በመፍጠር ከአንድ ቢሊዩን ብር በላይ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማስተሳሰር ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 133 ግንቦት 14 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!