<<ሦስት>>

Views: 576

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሙዚቃው ዓለም ሥማቸው እየገነነ ከመጡ ሙዚቀኞች መካከል ሮፍናን በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳል። በልዩ አዘፋፈን ስልቱ የሚታወቀው ይህ ሙዚቀኛ ባለፈው ሳምንት 16 ደቂቃ የሆነ ያልተለመደ ድንቅ የተባለለትን  <<ሦስት>> ሙዚቃ ይፋ አድርጓል። ሥራው የብዙዎች መነጋገሪያ ከመሆኑ አንፃር አዲስ ማለዳ ግጥሙን አንባቢያን እንዲያገኙት እንዲህ አቅርባዋለች።
የ30 ዓመቱ ሮፍናን የመጀመሪያ አልበሙን ከ3 ዓመት በፊት ለአድማጭ አቅርቧል። ስድስት ዓመት የፈጀበትን አልበም እንዳወጣ ወደ ዝና ማማ የወጣው ይህ የሙዚቃ ባለሙያና አቀንቃኝ በአጭር ጊዜ ታዋቂነትን ለማትረፍ የቻለ ነው።
ለቤተሰቦቹ ዘጠነኛ ልጅ የሆነው ሮፍናን ስሙን ያገኘው ከአባቱ እንደሆነ ይናገራል። ከጥልቅ ጸሎት በኋላ ሮፍናን ብለው ቢሰይሙትም ትርጉሙ ምን እንደሆነ ግን አይታወቅም።
በ10 ዓመቱ ለጓደኞቹ ካዜመ በኋላ ወደ ሙዚቃው ዓለም የገባው ሮፍናን ኑሪ ገና በ16 ዓመቱ ነበር የመጀመሪያውን ሙዚቃ ያዘጋጀው።
በሙዚቃው ዓለም በዲጄነት፣ በአቀናባሪነት፣ በጊታር ተጫዋችነት፣ በሬዲዮ አቅራቢነትና በሙዚቃ አዘጋጅነት እንዲሁም በግጥም ፀሃፊነቱ ይታወቃል።
ይህን ሁሉ ብቃቱን ተጠቅሞ ሙዚቃን በኤሌክትሮኒክስ መንገድ አቀናብሮ በአጭር መንገድ በብዙዎች ልብ ውስጥ መግባት ችሏል።

ሰው ነህ ይላል

የሀገሬ ልጅ
ስም አገኘሽ ወይ?
የሀገሬ ልጅ
ማን ነኝ አልሽ ይሆን?
እኔስ ልቤ እውነት አየ
ማን እንደሆንኩኝ ለየ
ነህ የተባልኩት እንዲገባኝ
ኋላዬን ዞር ብዬ ብቃኝ
ስሜ ተጽፎ አየሁት በክብር ቃል
ሰው ነህ ይላል
ከቋንቋ በፊት
ከዘር ቀድሞ ተጽፏል
ሰው ነህ ይላል
ከሀይማኖት ባህል
ከእምነትም ይቀድማል
ሰው ነህ ይላል
ቀድሞ ስላሴን ሸዋ ምኒልክ ቴዎድሮስ ሳይደግም
ግራኝ ሳይከትም ጉዲት ሳትጥል በቁም አክሱምን
ቀድሞ ቢላልን ቀድሞ አዛኑን ነብይ መላኩን
ቀድሞ ያሬድን ሦስቱ ዝማሬን በልጅ መዳንን
ንግሥተ ሳቢት ሳትይዝ ስንቋን ለሲና የሚሆን
ሳትጓዝ ልታይ የአምላክን ሥራ ጥበብ ሰለሞን
ጠቢቡም ሳይዘምም
ምኒልክ ሳይቀድም ፅላት ሳይከተል
ከሁሉ በፊት በሀገሬ
ኸረ ማን ነበር ዓለሜ
ጦቢያ እናት አለም የአለም ብርሃን
ጊዮን ሚዞርሽ የነፍስ እጣን
ሙሴ ለዮቶር ልጅ የበቃብሽ
ቅድሚያ እሱ ነጻ የወጣብሽ
ምድርም ታሪኳ ቢዘረጋ
ሀ ብሎ ሚጀምር ዘፍጥረት አንቺ ጋር
እምነት ታሪኳ ቢጻፍላት
አንድነት ተገኙ ናጋሺና ጽላት
ዛሬ አንተ ሰው ማነህ? አንተ ሰው ማነህ? ብለው ጠየቁኝ
የማነኝ ልበል ከአንቺ መፈጠር ብዙ አድርጎኝ
ያ ሰው ስም ያውጣ ያውቅበታል
የልጁ ማገር ነው የአባት ቤት ይመታል
ያ ሰው ስም ያውጣ ያውቅበታል
የልጁ ሰው መሆን የአባት ቤት ይበቃል
የሀገሬ ልጅ
ስም አገኘህ ወይ?
የሀገሬ ልጅ
ማነኝ አልክ ይሆን?
እኔስ ልቤ እውነት አየ
ማን እንደሆንኩኝ ለየ
ነህ የተባልኩት እንዲገባኝ
ኋላዬን ዞር ብዬ ብቃኝ
ስሜ ተጽፎ አየሁት በክብር ቃል
ሰው ነህ ይላል
የእናቴ መቁጠሪያ ዞር ዞር
የወጣው ልጇ ሰላም ጤና እንዲሆን
በይ እናት አለም
ጸሎትሽን ከእኔ ላይ ቀንሰሽ ለኢትዮጵያ አድርጊ
እኔ እንድኖር
አለዚያማ
ቢደርስልኝ ያንቺ ፀሎት እማ
ለብቻዬ ያለሀገርእማ
አልኖርማ
አንቺ ያየሽውን አላይ እማ
እውነት እውነት ጸሎትሽ ላይ ሀገር ጨምሪበት
የኔ ትውልድ ሰው እንዳይሆንበት
አጎንብሶ ሄደ ከአንገት እና ከጀርባው ዘር ጭነውበት
አይቼ እንዳላየሁ ሆድ ከሀገር ይሰፋል ብዬ እያለፍኩት
ማነህ? ብለው እነ ሆድ ከሀገር ይበልጣል ልቤን አስጨነቁት
ያ ሰው ስም ያውጣ ያውቅበታል
የልጁ ማገር ነው የአባት ቤት ይመታል
ያ ሰው ስም ያውጣ ያውቅበታል
የልጁ ሰው መሆን የአባት ቤት ይበቃል
ሰው ነህ ይላል
ባለሀገርነት ይህ ነው
ሰው ሀገሩ እግዚአብሔር ነው
እግዜር ሀገሩ ፍቅር
ፍቅር ግን የለው ሀገር
ፍቅር ሳይኖረው ሀገር
ሀገሬ አንቺን ሳፈቅር
የፈጠረኝ እንዳለው
ሰው አታድርጊኝ ምነው
የፍቅር ቃል አያልፍ ዘንድ አለም ያልፋል
ከአንቺ በፊት ነበር ስሜ ሰው ነህ ይላል
ፍቅር ሳይኖረው ሀገር
ሀገሬ አንቺን ሳፈቅር
ለፍቅር ቦታ ከሌለሽ ከበር እግዜርን መለስሽ።

ጥያቄ

ከአለም በፊት ከሀገር እና ሰው
በፈጠረን ፊት ሚበልጥ ማነው?
ጥያቄ
በፈጠረን ፊት ከበለጠ ሰው
እንደአምላክ ባስብ ስህተቱ የት ነው?
ጥያቄ
የቱን ባስቀድም ሰው ወይስ ሀገር
የሀገሬ ነገር ይሞላ ነበር?
ጥያቄ
ሀገሬን ሀገር ካደረገማ
ሰውን ላስቀድም ሰው ልሁንና
እንደ አድዋ እንደዚያ ሰሞን
ሀገሬ አማረች ሰው ለሰው ሲሆን
ለካ አድዋ ለሰው ልጅ ነበር
ለነጻነቱ የሆነው ሀገር
አሉ ምኒሊኩ
መልዕክቱን ሲልኩ
ሚስትህን ሚቀማህ
ማህተብ የሚያወልቅ
ልጅህን ሊወርሰው
ማንነት ሊያርቅህ
ባሪያው ሊያረግህ
ቆሟል ከደጅህ
ሀገርህ ሚስትህ ናት
ደግሞም እናትህ
ሀገርህ ልጅህ ናት ደግሞም ማህተብህ
ሰው ሆይ ተከተለኝ ሰው አርገኝ ላርግህ
ሰው አርገኝ ላርግህ
እናስ ይህ ምን ይላል?
ሀገር ሲተነተን የሰው ልጅ ይሆናል
ይሆናል
አድዋን ለሀገር ያደረገው ማነው?
አድዋ ለሰው ልጅ
አድዋ ለኔ ነው
የኔ ነው
ሚስትም ት….ሁን እናት ልጅም ማለት ሁሉም ሰው
የሂጃብም የማህተብም ተስፋው ማሰሪያው ሰው ነው
ድንግሏም እርሱም የሰው ልጅ
ሰው ጠልተው ማህተቡ ላይበጅ
ሰው ላፍቅር ጀግና ልሁን እና
ልቤ ላይ ነው የዛሬ አድዋ
ሰከላ አባይን ወለደች እናቴም እኔን
አድዋ ከራስ ጀመረ
እራሱን ያሸነፈ
ለሰው ተረፈ
ሁሉም ትውልድ አድዋ አለው
የኔም አድዋ ልቤ ላይ ነው
ጀግና ማለት
ይቅር ባይ ነው
ቂም በሆዱ ከሰበቀ
ጎጃም ሰው ካላረቀ
ከይቅርታ
ከራቀ
በላይ መቼ ዘለቀ
ይቅር ካላወቅንማ
ዮሀንስ ለሀገር ወድቆ ሲሰዋ
ቴዎድሮስ መቅደላ የጠጣት ጽዋ
ለከንቱ ነዋ
ባልቻ ዛሬም ይነፍሳል
አሉላ ዛሬም ይደርሳል
ቃል እተማዘዝነ
እኛው በእኛው አንሰን ከተራከስነ
በእነሱ አድዋ ድል አርገናል
ግን የኛን አድዋ ተሸንፈናል
ተው
አድዋን ለሀገር ያደረገው ማነው?
አድዋ ለሰው ልጅ
አድዋ ለኔ ነው
ሁሉም ትውልድ አድዋ አለው
የኔም አድዋ ልቤ ላየይ ነው
ጀግና ማለት
ዛሬ
ይቅር ባይ ነው።
ሰከላ አባይን ወለደች እናቴም እኔን

ሰከላ

ኢትዮጵያውያኖች እንደምን አላችሁ
የአንዲት እናት ልጆች ባዕድ የሌለባችሁ
ተው ተው ተው
እሯ እላለው እሯ በልዬ
የዚያ ጀግና ልጅ የዚያ ሰውዬ
እሯ በል አንተ እሯ በልዬ
የዚያ ጀግና ልጅ ግባልኝ
ይህ ይድረሰው ለዚያ ሰው
ወራሪውን ለመለሰው
የነጻነት ተምሳሌት አድርጎ
ስሜን ክብር ላለበሰው
ያረክልኝ ብዙ ነው
ከፍዬም የማልጨርሰው
ያረክልኝ ሁሌ አዲስ ነው
በሄድኩበት የምለብሰው
ብጠራው ስምህን
ጀግናውን ስራህን አመት መቼ ይበቃል
በአለም ያለ ጥቁር
ከትውልድ ትውልድ አንተን ያመሰገናል
እሯ ልበላ እንደአንተ ምንም እንኳን ከአንተ ባያምርብኝ
ዛሬ ላይ ምጽፈው የኔ የሚሆን ታሪክ ጨለማ ቢመስልብኝ
ተስፋ አለመቁረጥን ከአንተ ተምሬያለሁ አደራህም አለብኝ
እሯ ልበላ እንደአንተ ምንም እንኳን ከአንተ ባያምርብኝ
ሰከላ አባይን ወለደች እናቴም እኔን
ቅድሚያ ሰው ደግመው ግን ማነህ ሲሉኝ
ኢትዮጵያ ነው ስሜ
አልወድቅም ለመድረስ እጄ ቢያጥርም
ከበላይ ባለዘልቅም
ባይመስልም አንዴ እንኳ አያቅተኝም
እንደ ቴድሮስ ባልደግም
እሯ እላለሁ እሯ በልዬ
የዚያ ጀግና ልጅ የዚያ ሰውዬ
እሯ በል አንተ እሯ በልልኝ
የዚያ ጀግና ልጅ ግባልኝ
ሰከላ አባይን ወለደች
አሀሀሀይ ጉማ
ጦቢያው ለይቅርታ ቅደም ቀድመህ እንዳትተው ድገም
ደግሞ ቢያስቀይምሀ መልስ
የአባትክን አደራ መልስ
ያኔ በላይ ይዘልቃል
ያንጊዜም ቴዎድሮስ ይደግማል
ያንጊዜም አሉላ ራስ ነው
ምኒሊክ ዛሬም ንጉስ ነው
በልልኝ አንተሰው በልልኝ አንተው ራስህ ላይ
ይቅርበል አንተ ሰው እሯ በልበት ጥላቻ ላይ
አድዋ ዘማች የልጅ ልጅ እኔና አንት አይደለን ወይ
ሮፍናን ዘምነገደ ጦቢያው የአንተም እንዲያ አይደለም
ወይ?
ሰከላ አባይን ወለደች እናቴም እኔን
ቅድሚያ ሰው ደግመው ግን ማነህ ሲሉኝ
ኢትዮጵያ ነው ስሜ
ከቶ አልቀረም ለመድረስ እግሬ ቢያጥርም
አብዲሳን ባልቀድምም
ሳይጨልም ሳይመሽ ለይቅርታ ላዝግም
ጣይቱን አልሰጥም
እሯ እላለሁ
የልብ አድርስ
የዚያ ጀግና ልጅ የዮሀንስ
እሯ በል አንተ እሯ በልልኝ
የጃጋማ ልጅ ግባልኝ
ሰከላ አባይን ወለደች እናቴም እኔን
ሁሉም ትውልድ አድዋ አለው
የኔምአድዋ ልቤ ላይ ነው
ቢገፉኝ ፍቅር ማሳየት
በይቅር ልቆ መገኘት
ያንጊዜ አብዲሳ ይደርሳል
በልቤም ባልቻ ይነፍሳል
ዮሀንስ ደሙ ወርቅ ነው
ላልከዳው ጴጥሮስ መልስ ነው
ጠበቁኝ በደም ርሰው
የጥፋት ጉድጓድ ምሰው
በሰባራቸው አፍስሰው
ሰባራ ሰንደቅን ይዘው
እንግዲህማ እኔ ልሻል
መርዙን በይቅርታ ልሻር
ከአባቶቼም ባይሆንልኝ
ከአያቶቼ አንድነት ልማር
እሯ ልበል የዛሬ ሰው
ፍቅር ፈስሶብኝ ልፈሰው
ልንተባተብ ጀግንነቱን
ከልቤ ላግኝ ምህረቱን
ሰከላ አባይን ወለደች እናቴም እኔን

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com