ዳሸን ባንክ አዲስ የደንበኞች የቁጠባ አገልግሎት አስተዋወቀ

Views: 203

ዳሸን ባንክ አዲስ ያስጀመረው አዲስ የደንበኞች የቁጠባ አገልግሎት “ዳሸን ዋልያ ዳረንጎት” ሲሆን፣ የቁጠባ ባህል እና የባንክ አጠልግሎት ተጠቃሚነት የሚበረታታ ነዉ ተብሏል። “ዳሸን ዋለያ ዳረንጎት” የሚል መጠሪያ የተሰየመለት ይህ አገልግሎት ዘላቂ የቁጠባ ባህል እና የባንክ አገልግሎት ማበረታቻ ከመሆኑ በተጨማሪ፣ ባንኩ ለደንበኞች ሰጦታ የሚበረክትበት አገልግሎት መሆኑ ተገልጿል።
አገልግሎቱ ደንበኞት በዳሸን ባንክ ሲቆጥቡ እና የዉጭ ምንዛሬ በባንኩ በኩል ሰጠቀሙ የሚገኙት የማበረታቻ ስጦታ ነዉ። ባንኩ ይህን አዲስ የደንበኞች አገልግሎት ከመጪዉ ሀምሌ 1/2013 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደርግ የባንኩ ዋና ስራ አሰፈጻሚ አሰፋዉ አለሙ ጠቁመዋል።
ደንበኛች አገልግሎቱን ሲጠቀሙ የሚገኙት ሽልማት እንደ ገንዘብ መጠኑ ይለያያል ተብሏል። እንዲሁም የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ግብይት ሲፈጽም ቅናሽ እንደሚደረግላቸዉ ተመላክቷል። “ዳሸን ዋልያ ዳረንጎት” የባንኩኝ ተቀማጭ የገንዘብ መጠን እንደሚያሳድግ ተጠቁሟል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com