በአዲስ አበባ ከተማ የንግድ፣ የገበያ ትንተና እና የተቀናጀ የመሬት አስተዳደር ስርዓት መረጃ አሰራር ተግባራዊ ሊደረግ ነው ተባለ

Views: 39

የአዲስ አበባ ከተማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ በከተማዋ የንግድ፣ የገበያ ትንተና እና የተቀናጀ የመሬት አስተዳደር መረጃ ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል አሰራር ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑን አስታውቋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ እና ከፍተኛ የከተማዋ አመራሮች በተገኙበት አዳዲስ የመረጃ ቴክኖሎጂዎች ትግበራ የመሠረተ ልማት ግንባታ ስራ የማሰጀመር መርሃግብር ተካሂዷል።
ህጋዊ የንግድ ስርዓት መዘርጋት እና ፍትሃዊ የመሬት አጠቃቀም እንዲኖር በቅድሚያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ የመሬት ልማት ማኔጅመንት መረጃ ስርዓት እንደሚያስፈልግ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብርሃም ስርሞሎ በበኩላቸው፣ ነዋሪዎች የተቀላጠፈ የመረጃ አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ በተደራጁ መረጃዎችን መሰረት የተለያዩ ውሳኔዎችን ለመወሰን እንደሚግዙ አመልክተዋል።
በተጨማሪም በከተማዋ የሚስተዋለውን የመሬት መረጃ አያያዝ ችግር ፣የመሬት ወረራ እና ብልሹ አሰራሮችን እንዲሁም ህገ ወጥ ንግድን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው አቶ አብርሃም ተናግረዋል።
ፕሮጀክቱ በህንድ ኩባንያ አማካኝነት ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መንገድ እንደሚሰራ እና 220 ሚሊዮን ብር እንደተበጀተለት የገለጹት አቶ አብረሃም በቀጣይ ዘጠኝ ወራት ውስጥ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ብለዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 135 ግንቦት 28 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com