የእለት ዜና

የምስረታ ፈቃድ የጠየቁ ባንኮች እስከ ስድስት ወር ብቻ በ500 ሚሊየን ብር ካፒታል መመስረት ይችላሉ

የብሄራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶክተር) እንደ አዲስ ለመከፈት ወደ 17 የሚጠጉ ባንኮች ከብሄራዊ ባንክ ፈቃድ ለመውሰድ እየተጠባበቁ መሆናቸውን ገልጸው በባንኩ በኩል በስድስት ወራት ውስጥ በ500 ሚሊየን ብር የተከፈለ ካፒታል መመስረት እንደሚችሉ እና ከስድሰት ወራት በኋላ ግን በአዲሱ የመመስረቻ ካፒታል አምስት ቢሊየን ብር እንደሚመሰረቱ ገልጸዋል።
ይናገር እነዚህ አዳዲስ ባንኮች በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ብቻ የሥራ ፈቃዳቸውን እንዲወስዱ ብሄራዊ ባንክ እንደሚያበረታታ እና በኢትዮጵያ ውስጥ የባንኩ ዘርፍ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ስለሚገኝ እንዲበረታታ እና እንዲስፋፋ እንፈልጋለን። አቅም የሌላቸው እና ተወዳዳሪ ያልሆኑ ባንኮች እንዲፈጠሩ ስለማንፈልግ እና ከጎረቤት አገራት ጋር የሚወዳደሩ ባንኮች እንዲኖሩን ስለምንፈልግ የባንኮች የመመስረቻ ካፒታልን ወደ አምስት ቢሊየን ብር አሳድገናል ሲሉ በዘምዘም ባንክ የመክፈቻ ስነስርዓት ላይ ተናግረዋል።
ዘምዘም ባንክ የመጀመሪያው ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ የሆነ ባንክ ሆኖ በ876 ሚሊየን ብር ካፒታል ሥራ ጀምሯል። ባንኩ “አሊፍ” የተሰኘ የመጀመሪያ ዋና ቅርንጫፉን በቦሌ ጋራድ ሲቲ ሞል ሕንጻ ላይ ሲስያመርቅ የብሄራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶክተር) የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አህመድ ሺዲ የፌዴራል እስልምና ጉዳዮች ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር እንደሪስ እንዲሁም ምክትል ፕሬዝዳንቱ እና የባንኩ መስራች አደራጆች እና የቦርድ አባላት ተገኝተዋል።
ባንኩ ከ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ የአክሲዮን ሽያጭ እንዳስመዘገበ እና ባጠቃላይ የባንኩን አክሲዮን የገዙ አባላቶች ቁጥር 11 ሺሕ መድረሱን የዘምዘም ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መሊካ በድሩ ገልጸዋል። በመክፈቻ ሥነስርዓቱ ላይ ተገኙት ብሄራዊ ባንክ ገዢ ይናገር ደሴ (ዶክተር) በበኩላቸው ዘምዘም ባንክ በኢትዮጵያ የባንክ ታሪክ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ የሆነ ባንክ ነው። ብለዋል የዚህ ባንልክ ፕሬዝዳንት ደግሞ ሴት በመሆኗ ባንኩን በብዙ መልኩ ታሪካዊ ያደርገዋል ብለዋል።
ባንኩ ለእስለምና እምነት ተከታየች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም የአራችን ሕዝቦች ክፍት ሆኖ አገልግሎት ይሰጣል ሲሉ ተናግረዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 135 ግንቦት 28 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!