የ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሠላም እንዲጠናቀቅ እየሠራ መሆኑን የአማራ ወጣቶች ማኅበር አስታወቀ

Views: 31

የአማራ ወጣቶች ማኅበር በ6ኛው አገራዊ ምርጫና የወጣቶች ሚና ላይ የሚያተኩር ውይይት በደብረ ብርሃን ከተማ አካሂዷል። 6ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ በሠላም እንዲጠናቀቅ ወጣቶች ጉልህ ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ በውይይቱ ተነስቷል።
የአማራ ወጣቶች ማኅበር ሊቀመንበር ወጣት አባይነህ ጌጡ ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅና የዜጎች ሠላም እንዲጠበቅ ወጣቶች ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብሏል። ምርጫው ከአገር ባለፈ የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ደኅንነት የሚረጋግጥበት እንደሆነም ገልጿል። የአዲስ አበባ ወጣቶች ማኅበር ሊቀመንበር ወጣት ዘነበ በለጠ፣ የአዲስ አበባ ወጣቶች ማኅበር ከአማራ ወጣቶች ማኅበር ጋር በመሆን በኮሮና ቫይረስ መከላከል፣ በአምበጣ መከላከልና ተፈናቃዮችን በመደገፍ ሰፊ ሥራ ማከናወናቸውን ተናግሯል።
ወጣቶች በሠሩት ሥራም ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ በማድረግ ለወገን ደራሽነታችንን አረጋግጠናል ብሏል። በምርጫው ወጣቶች በንቃት በመሳተፍም ሠላማዊ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሊሠሩ እንደሚገባ አስገንዝቧል።


ቅጽ 3 ቁጥር 135 ግንቦት 28 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com