በ26 ምርጫ ክልሎች ሰኔ 14/2013 ምርጫ አይካሄድም

Views: 43

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ በ26 ምርጫ ክልሎች ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ድምጽ የመስጠት ተግባር እንደማይከናወን አስታወቀ። ቀደም ሲል በግንቦት 14/2013 ባወጣው መግለጫ በዕለቱ የድምጽ አሰጣጡ የማይከናወንባቸው ምርጫ ክልሎች መኖራቸውን እና ምክንያታቸውን አብራርቶ ነበር።
ስለምርጫ ክልሎቹ በየጊዜው ግምገማ እያደረገ ተጨማሪ ማብራሪያዎችን እንደሚሰጥ የገለጠው ምርጫ ቦርድ፣ ትናንት ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥቷል። በማብራሪያው 26ቱ የምርጫ ክልሎች በአራት የአገሪቱ ክልሎች የሚገኙ መሆናቸው ተጠቅሷል። እነሱም በቤንሻንጉል ክልል አራት ምርጫ ክልሎች፣ በኦሮሚያ ክልል ሰባት ምርጫ ክልሎች፣ በአማራ ክልል ስምንት ምርጫ ክልሎች እንዲሁም በደቡብ ክልል ሰባት የምርጫ ክልሎች በድምሩ 26 የምርጫ ክልሎች ናቸው።
ከዚህ በተጨማሪም፦ በሶማሌ ክልል ከ14ቱ ምርጫ ክልሎች 11ዱ ምርጫ ክልሎች ምርመራ ላይ እንደሚገኙ ተጠቅሷል። በተጠቀሱት 11ዱ ክልሎች ሰኔ 14/013 ድምጽ የመስጠት ሂደት ለማካሄድ አስቸጋሪ ይሆናሉ ተብሏል። በ11ዱ ምርጫ ክልሎች «ድምጽ መስጠት ሊከናወንባቸው የሚችል ምርጫ ክልሎች ካሉ» ምርጫ ቦርድ «ለይቶ የሚያሳውቅ» መሆኑን ገልጧል። ቦርዱ በየጊዜው ግምገማዎችን እንደሚያደርግ በመግለጥ የግምገማዎቹን ውጤቶች አሳውቃለሁ ብሏል።


ቅጽ 3 ቁጥር 135 ግንቦት 28 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com