የታክስ ክፍያ በበይነ መረብ መክፈል ተጀመረ

Views: 354

የታክስ ክፍያ በባንክ በኩል እንዲሆን የሚያስችል ኢ-ታክስ የተሰኘ አዲስ ቴክኖሎጂ በገቢዎች ሚኒስቴር ይፋ ሆነ። የገቢዎች ሚኒስቴር በዛሬው እለት ይህንን ኢ-ታክስ ተግባራዊ ከሚያደርጉ 5 ባንኮች ጋር ስምምነት አድርጓል። ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር ስምምነት የሚያደርጉት እነዚህ ባንኮች ብርሀን፣ ዳሽን፣የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ህብረት እና አዋሽ ሲሆኑ በቀጣይ ከሁሉም ባንኮች ጋር ለመስራት ታቅዷል።

በሀገራችን የሚገኙ ታክስ ከፋዮች ያለባቸውን ጫና ይቀንሳል የተባለለት አዲስ የቴክኖሎጂ ስርአት በዛሬው እለት በይፋ ስራ ጀምሯል። ይህ ሲስተም የባለሀብቶችን መረጃዎችን በሚፈለግበት ሁኔታ በማስቀመጥ ግብር ከፋዮች ግልጽ በሆነ መንገድ የሚሰራ አዲስ ቴክኖሎጂ ነው።
በስምምነት ዝግጅቱ ላይ የህብረት ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ መላኩ ከበደ፣ የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጸሀይ ሽፈራው፣ የዳሽን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አስፋው አለሙ፣ የብርሀን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አብረሀም አላሮ ፣ የገቢዎች ሚኒስቴር ዲኤታ ዘመዴ ተፈራ እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዘዳንት ዮሐንስ ሚሊዮን ተገኝተዋል። የኢ-ታክስ አገልግሎትን ከ2 አመት በፊት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተግባራዊ ሲያደርግ መቆየቱ ተገልጿል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com