የእለት ዜና

የኮንትሮባንድ ዕቃ በነዳጅ ቦቴ ሲጓጓዝ ተያዘ

በነዳጅ ቦቴ 150 ቦንዳ ወይም 11250 ኪ.ግ. የሚመዝንና 1 ሚሊዮን 406ሺህ 250 ብር ግምታዊ ዋጋ የሚያወጣ ልባሽ ጨርቅ ተጭኖ ሲጓጓዝ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።
ተሸከርካሪው የኮንትሮባንድ ዕቃ እንደጫነ በማረጋገጣቸው አሽከርካሪውና ሌላ አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር እንደዋለ በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ኬላዎች የሥራ ሂደት አስተባበሪ አቶ ዋሪዮ ጉዮ ገልጸዋል።
በአቃቂ ኬላ በኩል ለማለፍ የሞከረው የታርጋ ቁጥሩ3 ኢት 74384 እና የተሳቢ ቁጥሩ 3 ኢት 22121 ተሳቢ የነዳጅ መጫኛ ቦቲ እንደወትሮው የጫነው ነዳጅ ሳይሆን የኮንትሮባንድ እቃ መሆኑን ለቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከሕብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት መያዝ ተችሏል።
እንደ አቶ ዋሪዮ ጉዮ ገለጻ ኮንትሮባንድ በአንድ አገር ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ውስጥ በመግባት አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድር አደገኛና መጥፎ ድርጊት በመሆኑ ኮንትሮባንድን ለመከላከል የሚመለከታቸው አካላትና ሕብረተሰቡ ከምንጊዜውም በበለጠ ተናበውና ተጠናክረው ይሰሩ ዘንድ ማሳሰባቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 136 ሠኔ 5 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!