የእለት ዜና

ፖለቲካ ፓርቲዎችና ዜጎች ለፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ተባለ

Views: 120

ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ዜጎች ምርጫው ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ድርሻቸው ከፍተኛ መሆኑን ተገንዝበው ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ተነግሯል፡፡ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝምና የአስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህር ታምራት ቸሩ(ዶ/ር) በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ ዜጎች የምርጫን ጠቀሜታ ሊገነዘቡ፤ መብታቸውን በመጠቀምም 6ኛው አገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል።
አጠቃላይ የምርጫው ሂደቱ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን የፖለቲካ ፓርቲዎች አባሎቻቸውን፣ ዕጩዎቻቸውንና ደጋፊዎቻቸውን ግንዛቤ በማስጨበጥ አበክረው ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ በኅብረተሰብ መካከል ጸብ እንዳይፈጠር ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ያሳሰቡት መምህር፣ የሕዝብ ለሕዝብ አንድነት እንዲጠናከርም አብሮ የመኖር እሴትን ከሚሸረሽሩ ተግባሮች እንዲቆጠቡ አባሎቻቸውን ማስተማር እንደሚኖርባቸውም መክረዋል፡፡ ለሕግ ተገዥ መሆንና የሕግ ጥሰቶች ሲኖሩ ለሚመለከተው አካል ማሳወቅና የሚገጥሙ ችግሮች ካሉ በውይይት መፍታት እንደሚያስፈልግም አሳውቀዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 136 ሠኔ 5 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com