የእለት ዜና

የህብረት ስራ ማህበራት በኢኮኖሚው ዘርፍ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ተባለ

Views: 100

በፋይናንስ ዘርፍ የገንዘብ ቁጠባና ብድር በገጠርና በከተማ እንዲስፋፋ በማድረግ ለአገር ኢኮኖሚ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን የኅብረት ሥራ ማኅበር ኤጀንሲ አስታወቀ።
የኅብረት ሥራ ማኅበራት የአገር ውስጥ የግብርና ምርቶች ግብይት ተሳትፎን ከ15 በመቶ ወደ 46 በመቶ ከፍ በማድረግ የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎችን ለማሳደግ ታቅዷል።
በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅት በተለያዩ ጊዜያት ላጋጠመው የምርት አቅርቦት እጥረትና የዋጋ ንረት በኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ማኅበራትን ለማደራጀትና ለመጠናከር በተደረገው ጥረት ከ23.3 ሚሊዮን በላይ ግለሰብ አባላትን ያፈሩ፣ ከ94 ሺሕ በላይ መሰረታዊ የኅብረት ሥራ ማኅበራት እና 395 የኅብረት ሥራ ዩኒየኖች፣ አራት የኅብረት ሥራ ፌደሬሽኖች ተደራጅተው ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል በማፍራት ከ21 ቢሊዮን ብር በላይ ቁጠባ ከአባላቶቻቸው ማሰባሰብ ተችሏል ተብሏል።
በኢትዮጵያ ለ13ኛ ጊዜ ‹‹ኅብረት ሥራ ለበለጸገች ኢትዮጵያ›› በሚል መሪ ቃል አገር ዓቀፍ የዓለም ኅብረት ሥራ ቀን ባሳለፍነው ሰኔ 5/2013 መከበሩ ይታወሳል።
በክብረ በዓሉ ለዘርፉ እድገት ትልቅ ድጋፍ ላደረጉ የምስጋና እና በቀጣይም ለኅብረት ሥራ ከፍተኛ ኃላፊነት ይወጣሉ ተብለው የታመነባቸው ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ ከፍተኛ ምሁራን እና አርቲስቶች ለቀጣይ አራት ዓመታት ማለትም ከ2014 እስከ 2017 የሚቆይ የአምባሳደርነት ሹመት ተሰጥቷል።


ቅጽ 3 ቁጥር 137 ሠኔ 12 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com