የእለት ዜና

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ለምርጫው ሰላማዊነት መጀጋጀቱን አስታወቀ

Views: 92

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ በክልሉ በሰላም እንድጠናቀቅ ዝግጅት ማጠናቀቁን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩ ሰኔ 10/2013 በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡
ምርጫ በአንድ አገር የህዝብ የስልጣን ባለቤትነቱንና ልዋላዊነቱን በተግባር የሚረጋገጥበት ነው። ይህ ሁነት ደግሞ ሰላማዊ እንዲሆን ፖሊስ ከፍተኛ ኀላፊነት አለበት። በመሆኑም 6ኛው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የአማራ ክልል ፖሊስ ዝግጅቱን አጠናቋል ሲሉ ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩ በመግለጫቸው አንስተዋል።
የክልሉ ፖሊስ ከምርጫ በፊት፣ በምርጫ ወቅት እና ከምርጫ በኋላ በሚከውናቸው ተግባራት ላይ በቂ ዝግጅት የተደረገ ሲሆን ለዚህም በየደረጃው የሚገኝ ሁሉም የፖሊስ ኀይል ኀላፊነቱን እንዲወጣ የሚያስችል መግባባት ላይ ተደርሶ ኮማንድ ፖስትም ተቋቁሟል ሲሉ ኮሚሽነሩ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።
የፖሊስ ኮሚሽኑ ከፍተኛ መኮንኖች በሁሉም ዞኖች ሆነው ድጋፍ እያደረጉ ሲሆን በቅድመ ምርጫው ሂደት እስካሁን ድረስ ከጥቃቅን ጉዳዮች ውጭ የጎላ ችግር አለመከሰቱን ኮሚሽነሩ አረጋግጠዋል።
በምርጫው ወቅት እና ከምርጫ በኋላም ቢሆን ህዝቡ ያላንዳች የፀጥታ ስጋት የሚፈልገውን በመምረጥ የተለመደ ተግባሩን እንዲያከናውን ለማስቻልና ስጋቶችን ለመቅረፍ ከህዝቡ እና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ሰፊ ስራ ተሰርቷል ብለዋል።
በመጨረሻም ኮሚሽነሩ ለምናደርገው ማንኛውም የፀጥታ ስራ ህዝቡ ከጎናችን እንዲሆን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 137 ሠኔ 12 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com