የእለት ዜና

የምርጫ ማስታወቂያን የቀደደው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ

Views: 98

ዕድሜው 50 አመት የሆነው ተከሳሽ አብዱራዛቅ አህመድ አሊ በ2011 ተደንግጎ የወጣውን የኢትዮጵያ የምርጫ፣የፖለቲካ ፓርዎች ምዝገባና የምርጫ ስነምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/11 አንቀጽ 158 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፣ የምርጫ ማስታወቂያን በመቅደዱ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 5ኛ ወንጀል ችሎት ተከሶ ቀርቧል።
ተከሳሽ የምርጫ ዕጩ ተወዳዳሪን የምርጫ ማስታወቂያ ለማጥፋት በማሰብ ግንቦት 27/2013 በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 05 ልዩ ቦታው አዲስ አበባ ሜዲካል ኮሌጅ አካባቢ ባነር ከተለጠፈበት ቦታ ላይ በድንጋይ ወርውሮ በመቅደድ እንዳያገለግል ያደረገ በመሆኑ በፈጸመው የምርጫ ማስታወቂያን የማጥፋት ወንጀል በዐቃቤ ሕግ ተከሷል።
ዐቃቤ ሕግም የሰውና ሠነድ ማስረጃዎችን በማጠናቀር ክስ ያቀረበ ሲሆን፣ ተከሳሹም ክሱ ደርሶት፣ ወንጀሉን መፈጸሙን አምኖ የተከሳሽነት ቃል የሰጠ በመሆኑ፣ ፍርድ ቤቱ ሰኔ 04/2013 በዋለው ችሎት ጥፋተኛ ያለው ሲሆን፣ ተከሳሹ ከዚህ በፊት የወንጀል ሪከርድ ስላልቀረበበት፣የቀደም የዘወትር ጸባዩ መልካም እንደሆነ በማስብ፣ ወንጀሉን ስለመፈጸሙ እና ጥፋተኛ ስለመሆኑ አምኖ ቃሉን መስጠቱን በቅጣት ማቅለያነት በመያዝ በሦስት ወር ቀላል እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።


ቅጽ 3 ቁጥር 137 ሠኔ 12 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com