የእለት ዜና

የድምጽ መስጫ ቀን ሥራ ዝግ እንዲሆን ተወስኗል

Views: 81

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የመጀመሪያ ዙር የድምጽ አሰጣጥ ሰኞ ሰኔ 14/2013 እንዲከናወን መወሰኑ ይታወቃል። የድምጽ መስጫው ሰኞ ቀን መሆኑ ለድምጽ አሰጣጡ ሲባል በዕለቱ ሥራ እንደማይኖር ቦርዱ አስታውቋል።
በዕለቱ የተመዘገቡ ዜጎች ሁሉ ድምጻቸውን ለመስጠት ይችሉ ዘንድ እና የደምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ያለምንም የጸጥታ ችግር ይከናወን ዘንድ ቦርዱ የሚከተሉት ተግባራዊ እንዲሆኑ የምርጫ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና ስነምግባር አዋጅ 1162/ 2011 አንቀጽ 161 የመተባበር ግዴታ መሰረት ለመንግሥታዊ እና ለማንኛውም መንግሥታዊ ላልሆኑ ተቋማት አሳውቋል።
ዜጎች ዕለቱን ለድምጽ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ የፌዴራል እና የክልል (ከሐረሪ እና ከሶማሌ ክልል ውጪ) መንግሥታዊ ተቋማት ሰኔ 14/2013 ሥራ ዝግ ይሆናል።
የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት፣ ሆስፒታሎች፣ የእለት ተዕለት አገልግሎት ሰጪዎች (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት…) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ የሚያከናውኑ ሲሆን፣ የመተባበር ግዴታው የእነዚህን ተቋማት እንቅስቃሴ መዝጋት አያስገድድም ተብሏል።


ቅጽ 3 ቁጥር 137 ሠኔ 12 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com