የእለት ዜና

የአረብ ሊግ በህዳሴው ግድብ ጉዳይ ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ኢትዮጵያ ለፀጥታው ምክር ቤት ደብዳቤ ፃፈች

Views: 92

የአረብ ሊግ በህዳሴው ግድብ ጉዳይ ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ኢትዮጵያ ለፀጥታው ምክር ቤት ደብዳቤ ፃፈች።

የአረብ ሊግ ለተባሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ እና ለፀጥታው ምክር ቤት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጣልቃ በመግባት የጻፈውን ደብዳቤ በመቃወም ኢትዮጵያ በምላሹ ለጸጥታው ምክር ቤት ተቃውሞዋን በደብዳቤ ገልጻለች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በግድቡ ዙሪያ በያዙት አቋም የአረብ ሊግ ጣልቃ መግባቱ ተቀባይነት የሌለው ነው በሚል በደብዳቤው ውድቅ አድርጎታል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለምክር ቤቱ በጻፉት ደብዳቤ የአረብ ሊግ የሶሰቱ አገራት የጋራ የሆነውን ጉዳይ የተባበሩት መንግስታት በማይመለከተው ጉዳይ እንዳይ እንዲያየው መጻፉ መንግስታቸውን እንዳሳዘነ ገልጸዋል፡፡

ይህም ሶስቱ አገራት የጋራ መፍትሄ ለማጀት በአፍሪካ ህብረት መሪነት የጀመሩትን ጥረት የሚያሳንስ እና የአፍሪካ ህብረት እና የአረብ ሊግ የመፍትሄው አካል ለመሆን የሚያደርጉትን ወዳጃዊ እና የትብብር ግንኙነት የሚጎዳ አካሄድ መሆኑንም አቶ ደመቀ ገልፀዋል፡፡

በደብዳቤው ላይም የአፍሪካ ህብረት ለኢትዮጵያ ፣ ለግብፅ እና ለሱዳን የጋራ ድርጅት በመሆን “ለአፍሪካ ተግዳሮቶች የአፍሪካ መፍትሄዎች” በሚለው ጽኑ እምነት የሚመራ የድርድር መድረክ እና የሶስትዮሽ መድረክን የሚያቀርብ መሆኑ ተመልክቷል ፡፡

በተጨማሪም ኢትዮጵያ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ግብፅ እና ሱዳን በድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሀብት አጠቃቀም በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ባላቸው መርሆዎች ተገዥ እንዲሆኑ እንዲያበረታቱ በደብዳቤዋ በድጋሚ ጥያቄዋን አስተላልፋለቸ፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com