የእለት ዜና

በነገሌ ምርጫ ክልል ተቋርጦ የነበረው ምርጫ ተካሄደ

በነገሌ ምርጫ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤቶች ባሳለፍነው ሃምሌ 1/2013 ምርጫ መካሄዱ ተገልጿል፡፡ በነገሌ ምርጫ ክልል ከ150 በላይ ታዛቢዎችና የምርጫ አስፈጻሚዎች ተመድበው ምርጫ ማስፈጸማቸው ተመላክቷል፡፡
በነገሌ ምርጫ ክልል ለክልልና ለተወካዮች ምክር ቤቶች ኹለት በግል፣ አንድ ከኢዜማ እንዲሁም አራት ከብልጽግና ፓርቲ ዕጩዎች ለውድድር መቅረባቸው ተመላክቷል። ሰኔ 14/013 ሊካሄድ የነበረው ምርጫ አንድ የግል ዕጩ ተወዳዳሪ ባቀረቡት ቅሬታ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔ እንዲቋረጥ መደረጉን የሚታወስ ነው፡፡ በምርጫ ክልሉ ስር ከሚገኙ 139 ምርጫ ጣቢያዎች መካከል ድምጽ ያልተሰጠባቸው 30 የምርጫ ጣቢያዎች ቦርዱ ሐምሌ 1/2013 ድምጽ እንዲሰጥ በወሰነው መሰረት መካሄዱ ተመላክቷል፡፡
ምርጫ ቦርድ ከሰኔ 14ቱ ምርጫ አስቀድሞ ባወጣው መግለጫ፣ በነገሌ ምርጫ ክልል በቀረበ አቤቱታ ምክንያት ድምጽ የመስጠት ሂደቱ እንደማይከናወን አስታውቆ የነበረ ቢሆንም፣ በዕለቱ 109 በሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫ ሲካሄድ ውሎ ነበር።
ቦርዱ በምርጫ ክልሉ ድምጽ እንዳይሰጥ ወስኖ የነበረው በቦታው የሚወዳደሩ አንድ የግል ዕጩ ተወዳዳሪ በድምጽ መስጫ ወረቀት ላይ ስማቸው አለመካተቱትን ተከትሎ ያቀረቡትን አቤቱታ በመቀበል ነበር።


ቅጽ 3 ቁጥር 140 ሐምሌ 4 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com