የእለት ዜና

የሲሚንቶ ግብይት ዋጋ ላልተወሰነ ጊዜ በነጻ ገበያ እንድሆን ተወሰነ

Views: 35

የሲሚንቶ አቅርቦትና ስርጭት ቀደም ሲል በነበረበት የግብይት መመሪያ እንዲሆን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከሐምሌ 7/2013 ጀምሮ መወሰኑን አስታውቋል።
በሲሚንቶ ግብይት ላይ ይነሱ የነበሩ ቅሬታዎችን ለመፍታት ሲባል መንግሥት ከዚህ ቀደም የሲሚንቶ ምርት ተደራሽነትን ለማስተካከል ሲያደርገው የነበረውን የክትትልና ቁጥጥር ተግባር አቁሞ ዋጋው በነጻ የግበይት ሥርዓት እንዲፈጸም ወስኗል።
ሚኒስቴሩ ውሳኔውን ያሳለፈበት ምክንያት ወቅቱ ክረምት በመሆኑ የፍላጎት ማነስ ስለሚከሰት፣ አምራች ኢንዱስትሪዎች፣ አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎች ሲሚንቶ ባልተጋነነ ዋጋ ለመሽጥ በመስማማታቸው እና ፋብሪካዎች የበኩላቸውን ቁጥጥር ከደንበኞቻቸው ጋር እንደሚያደርጉ በማሳወቃቸው እንደሆነ ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም የፋብሪካዎችን አቅም በማጠናከር በአቅርቦት ላይ ያለውን ክፍተት ለመሙላት በመታቀዱና መንግሥት እንደ አስፈላጊነቱ ሲሚንቶ ከውጭ ለማስመጣት በመወሰኑ የግብይት መመሪያው ላልተወሰነ ጊዜ እንዲነሳ ተደርጓል።
ከሐምሌ 7/2013 ጀምሮ ቀደም ሲል የወጣው መመሪያና የማስፈጸሚያ ሰርኩላሮች በመሻራቸው፣ ሲሚንቶ በነጻ የገበያ ሥርዓቱ መሰረት ግብይቱ እንዲፈጸም ሚኒስቴሩ መወሰኑን ተከትሎ የዋጋ ንረት እንደታየ እየተገለጸ ነው። የሲሚንቶ አቅርቦት እጥረትና የዋጋ ንረት በግንባታ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን እንዳጓተተ በየቦታው ሲገለጽ እንነበር የሚታወስ ነው።


ቅጽ 3 ቁጥር 141 ሐምሌ 10 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com