የእለት ዜና

ምርጫ ቦርድ በገለልተኝነት መሥራቱ የሚመሰገን ነው ተባለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የምርጫ ሂደቱን ገለልተኛ በሆነ መንገድ ለማከናወን የሄደበት ርቀት የሚደነቅ መሆኑን በምርጫው በዕጩነት የተወዳደሩ ፖለቲከኞች ገለጹ።
ምርጫው ካለፉት አምስት ምርጫዎች በተሻለ መልኩ አሳታፊ እንደነበርም ነው የተናገሩት። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ውጤት ባለፈው ቅዳሜ ይፋ አድርጓል። በመርሃ ግብሩ በግልና የፖለቲካ ፓርቲ ወክለው በምርጫው በዕጩነት የተሳተፉ ግለሰቦች ምርጫን በሚመለከት ያላቸውን ልምድ አቅርበዋል።
የግል ተወዳዳሪ አለሳ ተሾመ ባለፉት ሰለሳ ዓመታት በኢትዮጵያ ነጻ፣ ፍትሐዊና ገለልተኛ ምርጫ ማካሄድ ፈታኝ ሆኖ መቆየቱን አስታውሰዋል። ከዚህ አንጻር ስድስተኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ትምህርት የተወሰደበትና የቦርዱ ገለልተኝነትም የተሻለ እንደነበር ተናግረዋል።
ከምርጫ ሕግና የቦርዱ አባላት አሰያየም ጀምሮ ያሉ በርካታ ጉዳዮች አሳታፊ እንደነበሩ ጠቅሰው፣ ምርጫው የአሸናፊ ተሸናፊ የዜሮ ድምር ባህልን መለወጥ የሚያስችል እንደሚሆንም ያላቸውን ዕምነት ገልጸዋል። ኢትዮጵያ አገራዊ ህልውናዋ ተጠብቆ እንዲቀጥል አንድ በሚያደርጉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
በተመሳሳይ በግል እጩነት የተወዳደሩት ብሩክ ይላቅና ገለሳ ዴሌቦ ምርጫው የዴሞክራሲ መሰረት የተጣለበት መሆኑን ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም በተካሄዱ አምስት ምርጫዎች መንግሥት “ምርጫ የሚመስል ድራማ ሲያካሂድ ቆይቷል” ሲሉም ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 141 ሐምሌ 10 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com