የእለት ዜና

በ10 የምርጫ ክልሎች ድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ ተወሰነ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎች ቅሬታን ተከትሎ በ10 ምርጫ ክልሎች የድጋሚ ምርጫ እና ውጤት ቆጠራ እንዲካሄድ መወሰኑን አስታውቋል።
በዚህም መሰረት ሰኔ 14/2013 በተካሄደው ምርጫ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎች ያቀረቡት ቅሬታ ከመረመረ በኋላ በ10 የምርጫ ክልሎች የተካሄደው ምርጫ እንዲሰረዝና በድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ ምርጫ ቦርድ ወስኗል።
ቦርዱ በድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ ከወሰነባቸው 10 የምርጫ ክልሎች ውስጥ በአማራ ክልል መርጦ-ለማሪያም፣ አዴት፣ ባቲ፣ ሞላሌ፣ ራያና ቆቦ ይገኙበታል። በአፋር ክልል ዳሎል የምርጫ ክልል፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መንጊ የምርጫ ክልል፣ እንዲሁም ደቡብ ክልል መስቃን ማረቆ፣ ቡሌና ባስኬቶ የምርጫ ክልሎች ናቸው ምርጫው ድጋሚ የሚካሄደው።
ቦርዱ ምርጫ ድጋሚ እንዲካሄድ ከመወሰን በተጨማሪ 10 የምርጫ ክልሎች ድጋሚ ቆጠራ እንዲካሄድ መወሰኑንም አስታውቋል።
ድጋሚ ቆጠራ እንዲካሄድባቸው ከተወሰኑ የምርጫ ውጤቶች ውስጥም 3ቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆናቸውን ነው ቦርዱ ያስታወቀው።


ቅጽ 3 ቁጥር 141 ሐምሌ 10 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com