የእለት ዜና

ከ30 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር ይዞ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

ከ30 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር ይዞ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ተጠርጣሪው የተያዘው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው 22 አንድ ተብሎ በሚጠራው ባቡር ጣቢያ ላይ መሆኑ ተገልጿል።

ግለሰቡ በወቅቱ 30ሺህ 204 የአሜሪካን ዶላር ይዞ ባቡር ሊሳፈር ሲል በባቡር ጣቢያው ላይ ተመድበው ሲሰሩ የነበሩ የፖሊስ አባላት ባደረጉት ፍተሻ ከነዶላሩ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

ህገ- ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የውጪ ሃገራት ገንዘቦችን በህገ- ወጥ መንገድ የመመንዘር ወንጀል የኑሮ ውድነት እንዲያሻቅብ ከማድረግ ባሻገር በሃገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ጫና ከፍተኛ በመሆኑ ህብረተሰቡ ይህንን ህገ- ወጥ ድርጊት ባለመፈፀም እና የሚፈፅሙ አካላትንም ለህግ አሳልፎ በመስጠት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንዲወጣ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል ።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!