የእለት ዜና

የእርዳታ እህል ወደ ትግራይ ለማጓጓዝ መቸገሩን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ

የተባበሩት መንግስታት ቃል አቀባይ ፋርሃን ሀቅ እንደገለጹት፣ መንገድ በመዘጋቱ ምክንያት በተሽከርካሪዎች ሲጓጓዝ የነበረውን የእርዳታ እህል ወደ ትግራይ ክልል ማስገባት እንዳልተቻለ ገልጸዋል።
ቃል አቀባዩ አያይዘው እንደተናገሩት፤ የእርዳታ ሠራተኞችን፣ ምግብ፣ ነዳጅ እና ሌሎች ሰብዓዊ አቅርቦቶችን የጫኑ ከባድ መኪናዎች ከሰመራ ከተማ ወደ ትግራይ በሚወስደው መንገድ ላይ ተዘግቶባቸው መንቀሳቀስ አልቻሉም፡፡ በዚሁ ችግር ምክንያት እርዳታ ለሚፈልጉ የትግራይ ክልል ተረጂዎች መድረስ አልተቻለም።
በቀጣይ ቀናት የረድኤት ሰጪ ሰራተኞችን እና እንደ ነዳጅ ያሉ አቅርቦቶችን ወደ ትግራይ ማስገባት ካልተቻለ አንድ አንድ ሰብዓዊ ድጋፎች እንደሚቋረጡም ያለውን ስጋት ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።
ድጋፉን በአውሮፕላን ለማድረግ በመንግሥት በኩል እድሉ እንደተመቻቸላቸውና ዕቅድ መያዙንም ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 142 ሐምሌ 17 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!