የእለት ዜና

የኢትዮጵያ ጠንካራ ሴቶች

“ሲቄ” የሚለው የኦሮምኛ ቃል ‹አለንጋ› የሚል ትርጉም አለው። በገዳ ትውፊታዊ አስተዳደር ውስጥ በባሏ ጥቃት የደረሰባት ሚስት፣ ከሌሎች ሴቶች ጋር በመሆን ባሏ ላይ የካሣ ውሳኔ የምታሳልፍበት ስርዓት ሲቄ ይባላል።

በ 1902 በድሮው አጠራር በከንባታ አውራጃ በሆሳዕና ከተማ አርበኛ ልክየለሽ በያን ተወለዱ።አርበኛ ልክየለሽ ለአቅመ ሄዋን ሲደርሱ እንደ አደጉበት ማኅበረሰብ ትዳር የመሰረቱት በልጅነት ጊዜአቸው ነበር።
አርበኛ ልክየለሽ በያን በ1928 ዓም ጣሊያን ኢትዮጲያን ዳግም በወረረችበት ወቅት የአያታቸውን የአቶ ሽብሩ ጤናውን ጠመንጃ አንግተው የከምባታን አውራጃ ጦር ይዘው ከዘመቱት ደጃዝማች መሸሻ ወልዴ ስር በሰሜን ኢትዮጵያ ተዋግተው እንደነበር ታሪክ ያወሳቸዋል። በተሳተፉበትም ጦርነት ላይ አርበኛ ልክየለሽ ከፍተኛ ሚና ነበራቸው።

ለኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ የአገራቸውን ጥቅም ለማሰከበር ብዙ ሴቶች ደማቸውን አፍሰዋል፤ አጥንታቸውን ከስክሰዋል። ከዚህም ባለፈ ሕይወታቸወን ያጡ በርካቶች ናቸው።
በቀደመው ጊዜ የነበሩ ጠንካራ ሴቶች በከፈሉት ዋጋ ያህል ክብር አልተሰጣቸውም። ብዙዎቹ ከማኅበረሰቡም ሆነ ከመንግሥት ዕውቅናን ሳያገኙ ማለፋቸው አይዘነጋም።
የነዚህ ጠንካራ ሴቶች ታሪክ ግን አሁን ላለው ተተኪ ትውልድ ተላልፏል ማለት አይቻልም። ሴቶችም ይህንን አኩሪ ተግባር እንደ ምሳሌነት ሲጠቀሙበት ማየት አልተለመደም።

ይሁን እንጂ በማኅበረሰቡ ዘንድ ሴቶች ለአገራዊ ድል ከተሳተፉበት አኳያ እንዲሁም ምሳሌ ሊሁኑ የሚችሉ ጠንካራ ሴቶችን ከማንሳትና ከማወደስ ይልቅ በቤት ውስጥ ሥራ ኃላፊነት መውሰድ ላይ ብቻ ያተከረ ሐሳቦች ሲነሱ ይስተዋላል።
ለአገራቸው ሲሉ የተሰዉ ጠንካራ ሴቶችን ታሪክ ማወደስ ያስፈላጋል። ለሴቶች እንደ አርአያ የሚነሱ ታሪክ ያላቸውን አንጋፋ ሴቶችን ማስታወስ ይጠቅማል።

በድሮ ጊዜ ሴትን ልጅ ትምህርት ማስተማር አያስፈልግም ብለው ከሚየምኑ የማኅበረሰባችን ክፍሎች በመውጣት በትምህርታቸውና በሥራቸው ስኬታማ የሆኑ ሴቶችን ለአሁኑ ትውልድ እንደ ምሳሌነት ማቅረብ ያስፈልጋል።
በአገራችን ያሉ የፊልም ደራሲዎች በፊልሞቻቸው የሴትን ልጅ ከብር የሚነኩ ተውኔቶችን ለማኅበረሰቡ ከሚያስተላፉ፣ የጠንካራ ሴቶችን ታሪክ ማወሳት እንዲሁም ለአለም ማስተላፍ ይኖርባቸዋል።
የጠንካራ ሴቶችን ተግባርና ታሪክ ለትውልዱ ለማስተላለፍ ኹሉም የማኅበረሰባችን ክፍሎች የድርሻቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል።

ከዚህም ጋር በተያያዘ ደራሲያን በድርሰታቸው፣ ዘፋኞች በግጥማቸው፣ ሰዓሊያን በስዕላቸው የኢትጵያን ጠንካራ ሴቶች ታሪክ ማውሳት 㙀ገራዊ ግዴታቸው ሊሆን ይገባል።
ይህን ታሪክ ለተተኪ ትውልድ በማስተላለፍ ሴቶች የራሳቸውን ታሪክ መመልከት ይችላሉ። በዚህም ምክንያት ሴቶች ከፍተኛ የሆነ የሞራል መነቃቃትን ያገኛሉ።

በኢትዮጵያ ባሁኑ ወቅት ሴቶችን በተመለከተ ከፍተኛ ለውጥ መጥቷል ። ሴቶችን በተለያዩ ሥልጣን ላይ ተቀምጠው ማየት ተጀምሯል። ሴቶች ያመኑበትን መንገድ በመከተል የራሳቸውን ሕይወት መምራት ጀምረዋል።
በትምህርት ቤት፣ መሥሪያ ቤት እንዲሁም በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ መሆን ችለዋል። ከዚህም በተጨማሪ ሴቶች በተሰማሩበት መስክ ብቁ፣ ጠንካራንና ኃላፊነት ወስደው የተሻለ ሥራ እንደሚሠሩ ማስመስከር ጀምረዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 142 ሐምሌ 17 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!