የእለት ዜና

“ኢትዮጵያ ከምርጫው በኋላ ሲኦል ትሆናለች ያሉ አፍረዋል” አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

“ኢትዮጵያ ከምርጫው በኋላ ሲኦል ትሆናለች ያሉ አገራትና 27 ዓመት ተከፋይ የነበሩ ሚዲያዎች አፍረዋል፤ አንዳንድ አገራትም አሁን ላይ ስለምርጫው እንኳን ደስ አላችሁ ማለት ጀምረዋል” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሐምሌ 14/2013 በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ ምርጫውን ምክንያት አድርገው ለግጭት የተመኙንም ሆነ ኹለተኛውን የሕዳሴ ግድብ ውኃ ሙሌት ካካሄዳችሁ በኢትዮጵያ ችግር ይፈጠረል ያሉ አገራት ከማፈር አልፈው፣አቋማቸውንም ቀስ በቀስ ቀይረዋል ብለዋል።
6ኛው አገራዊ ምርጫ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መሆኑን መሰረት በማድረግ የተለያዩ አገራት መሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የደስታ መግለጫ ማስተላለፋቸውን ገልጸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ተወካይ ጋር ተገናኝተው ውይይት ማድረጋቸውንም ነው የተናገሩት። በውይይታቸውም 6ኛውን አገራዊ ምርጫ፣ ታላቁ የሕዳሴ ግድብና የትግራይ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ገለጻ መደረጉን አንስተዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 142 ሐምሌ 17 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com