የእለት ዜና

የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ዕጩ በመተከል ተገደለ

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚንቀሳቀሰው የቦሮ ዴሞክራሲያዊ(ቦዴፓ) ዕጩ ተወዳዳሪ በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ ላይ መገደሉን ፓርቲው አስታወቀ። በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ምርጫ ክልል፣ ቦዴፓን ወክሎ ለክልል ምክር ቤት ለመወዳደር በዝግጅት ላይ የነበረው አይናድስ ሞላ በግልገል በለስ ከተማ ሙቶ ተገኝቷል ተብሏል።
ሞቶ የተገኘው ዕጩ የአሟሟቱ ሁኔታ እየተጣራ እንደሆነ የጠቆመው ፓርቲው፣ ለድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎች፣ ለቤተሰቡና ወዳጆቹ መጽናናትን ተመኝቷል።
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን በተፈጠረው የጸጥታ ችግር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዞኑ ሰኔ 14/2013 ምርጫ ማካሄድ አልችልም ማለቱን ተከትሎ ምርጫ የፊታችን ጳጉሜ 1/2013 እንደሚካሄድ ይጠበቃል። በጸጥታ ችግር ምርጫው የተራዘመበት መተከል ዞን አሁን ላይ ያለው የጸጥታ ሁኔታ መሻሻል እንዳላሳየ እና የዜጎች ግድያ እንደቀጠለ ፓርቲው ጠቁሟል።


ቅጽ 3 ቁጥር 142 ሐምሌ 17 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!