የእለት ዜና

ታታሪ የኢትዮጵያ የኢንደስትሪ ፓርኮች ሰራተኞችን ተጠቃሚ ማድረግ አላማው ያደረገ የቁጠባ እና ብድር ፕሮግራም በይፋ ተጀመረ

ታታሪ የኢትዮጵያ የኢንደስትሪ ፓርኮች ሰራተኞችን ተጠቃሚ ማድረግ አላማው ያደረገ እና በማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ብሪጅስ ፕሮግራም የተደገፈ፤ የቁጠባ እና ብድር ፕሮግራም የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮምሽነር ዳንኤል ተሬሳ በተገኙበት በሀዋሳ ከተማ በይፋ ተጀምሯል፡፡

ፕሮግራሙ የስራተኞችን በየጊዜው ስራ የማቆም እንዲሁም ምርታማነትን የመቀነስ ችግሮችን ለመቀረፍ ይረዳል ተብሎ የታመነበት ሲሆን ፕሮግራሙ እውን እንዲሆን የፌዴራል እና የክልል መንግስታት ተቋሞች፣ ፋብሪካዎች እና የፋብሪካ ሰራተኞች፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲሁም የሃዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ ኢንቨስተሮች ማህበር ትልቁን ሚና እንደሚወስዱ በሁነቱ መገለፁንም ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!