የእለት ዜና

በመተከል ዞን ወምበራ ወረዳ የመንግስትን ጥሪ አልቀበልም በማለት በሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላም ሃይሎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

በመተከል ዞን ወምበራ ወረዳ ግዳጁን በመፈፀም ላይ የሚገኘው የ2211ኛ ሻለቃ ሰራዊት አባላት የመንግስትን ጥሪ አልቀበልም በማለት በሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላም ሃይሎች ላይ እርምጃ መውሰዱኝ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ፡፡

የ2211ኛ ሻለቃ ዋና አዛዥ ሻለቃ ዮሃንስ እውነቱ እንደተናገሩት ፣ ከሀገር ሰላም በተቃራኒ በመሆን እና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ወደ ጎን በመተው ህዝቡ በሰላም ወጥተው በሰላም እንዳይገባ የጥፋትን ሰራ እየፈፀሙ ባሉ ሃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ 25 የሽፍታ አባላትን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ማርኳቸዋል ተብሏል፡፡

ጠላት ታጥቆ ስንቀሳቀስ የነበረውን ዘጠኝ ክላሽ መሳሪያ፡ ሶስት ኋላ ቀር መሳሪያ እንዲሁም በርካታ የድምፅ አልባ መሳሪያ ወይም ቀስቶችን መማረካቸውንም አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም 185 የክላሽ ጥይት ፡ 16 የብሬን ጥይት እና አንድ የእጅ ቦምብ ይዘው በህብረተሰቡ ላይ ጥቃት ለማድረስ ቢያስቡም ሰራዊቱ ቀድሞ በመንቃት በጠላት ላይ ድል መጎናጸፋን ነው መግለጻቸውን ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!