የእለት ዜና

በአፋር ክልል የዳሊኮሞ በተባለ ቦታ ከ10ሺህ በላይ ተፈናቃዮች በመኖራቸዉ አፋጣኝ እርዳታ ተጠየቀ

በአፋር ክልል የዳሊኮሞ በተባለ ቦታ ከ10ሺህ በላይ ተፈናቃዮች በመኖራቸዉ የክልሉ የአደጋ መካላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አፋጣኝ እርዳታ ጠየቀ፡፡

በአማራና በትግራይ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች በህወኃት በተከፈተ ጥቃት ከ70ሺህ በላይ ነዋሪዎች ቀዬአቸውን ለቀው መውጣታቸ የሚታወስ ነው፡፡

የተፈናቀሉ ሰዎችን ወደ ሁመራ፣ ሎጊያ እና ተፈናቃዮቹ የሚያስጠጉን ዘመዶች አሉን ወዳሉበት ቦታ እንዲጠለሉ ተደርጓል ተብሏል፡፡

ሆኖም ካለው የተፈናቃይ ብዛት አንፃር በቂ መጠለያ መስጠት እንዳልተቻለ የአፋር ክልል የአደጋ መካላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሃላፊ አቶ ማሂ አሊ ተናግረዋል፡፡

በተለይም የዳሊኮም በተባለ ስፍራ ባለ ቀበሌ 10 ሺህ ተፈናቃዮች በመኖራቸው ለተፈናቃዮች የሚደረጉ የሰብዓዊ ድጋፎች በአፋጣኝ እንዲደርስ በክልሉ ባሉ አለም አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ አስተባባሪዎች እና በፌደራል ደረጃም የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አፋጣን ምላሽ እንዲሰጥ ተጠይቋል ብለዋል፡፡

የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አፋጣኝ ምላሽ መስጠት መጀመሩን ሃላፊው አስታውቀዋል፡፡

ለተፈናቃዮች የዱቄት እና የብርድ ልብስ ድጋፎችንም በተቻለ አቅም ለማድረስ እየተሞከረ ቢሆንም በቂ አለመሆኑን መናገራቸውን አሐዱ ዘግቧል፡፡

 

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!