የእለት ዜና

ተፈናቃዮች ወደ ወረዳዎች የተመለሱ ሲሆን አንዳድ አካባቢዎች ከሚፈጠሩ መጠነኛ ግጭቶች ውጪ ሞትና መፈናቀልን ማስቀረት ተችሏል፡- ብ/ጄኔራል አለማየሁ ወልዴ

ተፈናቃዮች ወደ ወረዳዎች የተመለሱ ሲሆን አካባቢዎች ከሚፈጠሩ መጠነኛ ግጭቶች ውጪ ሞትና መፈናቀልን ማስቀረት መቻሉን ብ/ጄኔራል አለማየሁ ወልዴ ገለጹ፡፡

በመተከል የተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ኃይል ኮማንድ ፖስት የተቀመጡለትን ግቦች በሚገባ ማሳካት መቻሉን የኮማንድ ፖስቱ አባል ብ/ጄኔራል አለማየሁ ወልዴ አስታወቁ፡፡

ጄኔራሉ በመተከል ዞን ለተሰማራው ሁለተኛው ዙር የሲዳማ ክልል ልዩ ኃይል አባላት ባደረጉት የግዳጅ ቀጣና ገለፃና የስራ መመሪያ ንግግራቸው ፤ ኮማንድ ፖስቱ የተሰጠውን ተልዕኮ በሚገባ መፈፀሙንና ግዳጁን ለመፈፀምም በርካታ መስዋእትነት መከፈሉን ተናግረዋል።

በዞኑ የሰው ሞትና መፈናቀልን ማስቀረት ፣ ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው መመለስና የህዳሴ ግድብን ቀጣና የሰላም ሁኔታ ማረጋገጥ የኮማንድ ፖስቱ ዋንኛ ተልዕኮዎች መሆናቸውን የጠቆሙት ጀኔራል መኮንኑ፤ ተፈናቃዮች ወደ ወረዳዎች የተመለሱ ሲሆን አንዳድ አካባቢዎች ከሚፈጠሩ መጠነኛ ግጭቶች ውጪ ሞትና መፈናቀልን ማስቀረት መቻሉን አስረድተዋል።

የዞኑ ዋና ከተማ የሆነው ግልገል በለስ ከተማ በግጭቱ ወቅት ወደ ህዳሴ ግድብ የሚደረገው የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ ተስተጓጉሎ እንደነበር አስታውሰው ፤ በተፈፀመው ስኬታማ ተልዕኮ ይህንን ሁኔታ መለወጥና ቀጣናውን ሰላማዊ በማድረግ የግድቡ ሁለተኛው ሙሌት በሰላም የተፈፀመበትን ሁኔታ መፍጠር ተችሏል ብለዋል ።

የሲዳማ ክልል ልዩ ሀይል ምክትል አዛዥ ኢንስፔክተር አሸናፊ ቴዎድሮስ በበኩላቸው ፣ “በዚህ ወሳኝ ወቅት የክልሉና የፌደራል መንግስታት ከባድ አደራ ጥለውብናል” ያሉ ሲሆን ራሳቸውን መስዋእት በማድረግ ህዝብና አገራቸውን ለማኩራት ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

የሰራዊት አባላቱም የሀገራችንን አንድነት በመፈታተን ልማታችንን ለማደናቀፍ የተነሳብንን የአሸባሪው ህወሀት ጁንታ ሴራ ከኢፌዴሪ መከላከያና ከፌደራል ፖሊስ ጋር በጋራ በመሆን እናመክናለን ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!