የእለት ዜና

ከ30 ሚልዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ለአፋር ክልል መደረጉ ተገለፀ

ከ30 ሚልዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ለአፋር ክልል መደረጉን ኡስታዝ አቡበክር አህመድ አስታውቀዋል።

ድጋፉ የሙስሊም AlD አሜሪካ ሰብዓዊ አገልግሎት ድርጅትን በማስተባበር የተደረገ ሲሆን ድጋፉ የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶችን እና መድሃኒቶችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

በኡስታዝ አቡበክር አህመድ አማካኝነት የተገኘው የህክምና መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ የክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊዎች እና የክልሉ መጅሊስ አመራሮች በተገኙበት ርክክብ ተደርጓል፡፡

ለተደረገው ድጋፍ የክልሉ መንግስት ከፍተኛ ምስጋናውን ያቀረበ ሲሆን ለሙስሊም AlD አሜሪካ ሰብዓዊ አገልግሎት ድርጅት እና ለኡስታዝ አቡበክር አህመድ የእውቅና እና የምስጋና የምስክር ወረቀት በክልሉ መጅሊስ ፕሬዝደንት አማካኝነት ማበርከቱም ታውቋል።

ከዚህ ቀደም ለሃላባ ዞን ከ 25ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉ የሚታወስ ሲሆን በወቅቱም ለአፋር ክልል መሰል ድጋፍ ለማድረግ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸው ተጠቅሶ እንደነበር ይታወሳል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!